በወያኔ ምክንያት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ይቁም!!! ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር/ኢሕአግ/ የተሰጠ መግለጫ

 

የኢትዮጵያ ህዝብ አገር ውስጥ በሚደርስበት ሰቆቃና ጫና ሳቢያ ለስደት እየተዳራገ ይገኛል። ህዝቡ በአገሩ ሰርቶ ለመኖርም ሆነ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለማስከበር አልቻለም። ኢትዮጵያ በታሪኳ ገጥሟት በማያውቅ መልኩ በኢኮኖሚውም ሆነ በሌሎችም ዘርፍ ውድቀት ውስጥ ገብታለች። ለዚህ ውድቀትና ድቀት ብዙ ምክንያቶችን መጠቃቀስ ይቻላል መሰረታዊው ምክንያት ግን ወያኔና ወያኔ ብቻ ነ ው። ከቀን ወደ ቀን ወደ ከፋ ደረጃ የሚገኘው የኑሮ ውድነት ዜጎች የእለት ጉርሳቸውን እንኳን ለመሸፈን አዳጋች   ሆኖባቸዋል። የኑሮ ውድነቱ እንደ እግር እሳት እያንገበገበው የሚገኘው ወገናችን ከዚሁ በተጓዳኝ በፖለቲካው በኩል ሃሳብን በነጻነት የማንሸራሸር፣የመደራጀት፣ የመብት ጥያቄዎችን የማቅረብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣የፈለገውን የመቃወምና የመደገፍ መብት፣ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት፣ የሰብዓዊ መብት መከበር … የመሳሰሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ህዝቡ በሚያቀርብበት ወቅትና ለመብቱ ፣ ለነጻነቱ፣ ለአንድነትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ በሚንቀሳቀስበት ወቅት በአምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ዘንድ እየተወሰደ የሚገኘው ኢ-ዴሞክራሲያዊና ኢ-ሞራላዊ የሆኑ ጭፍን እርምጃዎች ምክንያት ህዝቡ ባገኘው አጋጣሚና ባመቸው መንገድ ሁሉ በየአቅጣጫው እንዲሰደድ አድርጎታል። ወያኔ ሰራሽ በሆኑ ችግሮች ተገዶ ስደት እንደ አማራጭ ወስዶ በሰው አገር እየተንከራተተ የሚገኘው ወገናችን ህመም እጅግ ያመናል ለመፍትሄውም በአገር ቤትና በስደት ከሚገኘው ወገናችን ጋር አብረን እንቆማለን። በአረብ  አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን የማንገላታ፣ የማሰር፣ የመደብደብና ለአካል ጉዳት የመዳረግ ብሎም በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል በየጎዳናው ዜጎቻችን እንደ አልባሌ እቃ ተጥለው ስንመለከት በቃላት ሊገለጽ የማይችል ልዩ ስሜት አእምሮአችን ላይ ፈጥሯል ። ጉዳዩ በግራም ተኬደ በቀኝ ከወያኔው ቡድን አለቆች ተጠያቂነት ጋር የተያያዘ ነው። ለአባይ ግድብ ግንባታ ቦንድ ግዥ ድንፋታ ወቅት ዲያስፖራው ገንዘብ እንዲያዋጣ በዓለም አገራት የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ ኪስ ለመበርበር ቁጥር ስፍር የሌለው ስብሰባ በማካሄድና ባዶ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት ውጭ የሚኖረውን ወገናችንን ጥሪት ለማግበስበስ ሲሯሯጥ የነበረው የወንበዴ ቡድን ዛሬ ወገኖቻችን በአረብ አገራት ቅጥ የለሽ በደል ሲፈጸምባቸው የኢትዮጵያ መንግስት ተብዬውና በአረብ አገራት የሚገኙ ኤምባሲዎች ምነው ዝምታውን መረጡ? እየፈሰሰ ያለው የንጹሃን ደምና ያለ አግባብ እየሞተ የሚገኘው ዜጎቻችን ጉዳይ አይቶ እንዳላየ ማለፉ ህዝባዊ ፍቅር ወገንተኝነትና ተቆርቋሪነት መንፈስ ጭራሽ ያልፈጠረባቸው መሆኑ ማረጋገጫ ነው። የሚገርመው ነገር የሚጠሉትን የኢትዮጵያ ህዝብ በግድ ካልመራንህ እያሉ ፍዳውን ማሳየታቸው ሲሆን ህዝብን በመናቅና በግብዝ አመለካከት አገርን እናስተዳድራለን ማለቱ ከንቱ አባዜ ነው ስለሆነም ድርጅታችን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በአረብ አገር ኑሮአቸውን ባደርጉ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ የወያኔው ቡድን መልካም አስተዳደር ባለመስፈኑ ምክንያት መሆኑን በጽኑ ያምናል። ኢሕአግ ዜጎቻችን ከተዘፈቁበት አደጋ እንዲወጡ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል ድርጅታችን ለተነሳለት ቅዱስ አላማ መሳካት በአገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን በጋራ እንድትነሱ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

 

 

አንድነት ሃይል ነው!

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር/ኢሕአግ/

ህዳር 6/2006 ዓ/ም

 

 

Search

Latest Articles

 1. 07-03-2006
  (1999-11-30 00:00:00)
 2. መግለጫ
  (1999-11-30 00:00:00)
 3. 05-03-2006
  (1999-11-30 00:00:00)
 4. 30-02-2006
  (1999-11-30 00:00:00)
 5. 23-02-2006
  (1999-11-30 00:00:00)

 
 
Advertisements
Posted in Uncategorized | Leave a comment

Herlig folkefest i Stavanger!

På det meste var det 300 til stede på lørdagens demonstrasjon for en rettferdig asylpolitikk. Bredt politisk spekter av Sv, V, Rødt og Krf holdt appeller. Redd Barnas ungdomsorganisasjon Press, støtteforeningen for Ethiopia og for Neda gjorde sammen med RIA en kjempeinnsats for å belyse ulike utfordringer Norge har for å kunne skilte med en rettferdig asylpolitikk. Rapperne Tore Pang og Bevis leverte høykvalitets rap. Det er rett og slett gøy å samles fra så mange hold med en felles sak. Her ser du bilder fra festen:

 

Vi vil ha NEDA og familien hjem:

DSC_0016

Annuler returavtalen med diktaturstyret i Etiopia:

 

DSC_0195

20131117-144455.jpg

20131117-144527.jpg

20131117-144906.jpg

20131117-144950.jpg

20131117-145057.jpg

20131117-231415.jpg

20131117-231630.jpg

Aside | Posted on by | Leave a comment

Kampen for 331 etiopere!

I to år har RIA hatt høyt trøkk i Etiopia saken. Her ser du hvorfor:

20131118-111417.jpg

 

For to år siden hadde Norge i overkant av 500 lengeventende etiopere. Noen hadde allerede da ventet i 12-17 år. Da RIA tok saken var det først og fremst for å si at en slik uavklart lang tid kan ikke Norge gå med på at noen i vårt land må gjennomgå. Vi kan ikke kalle oss et land bygd på kristen og humanistisk arv og la folk gjennomgå betydelige traumer av å aldri kunne begynne livet på nytt. ( se grunner for ventetid nederst i artikkel)

Istdenfor å rydde opp på en human måte, svarte den rød/grønne regjering med å inngå returavtale med despotene i Ethiopia. En absurd relasjon oppstår med et regime Norge vanligvis vil nekte å handle med. Nå skal uttalte fiender av regimet sendes rett tilbake til landets fryktede sikkerhetspoliti, gjennom en avtale som mangler oppfølgingskrav. Slike har man med f.eks flere land gjennom IOM, men med overgriperne i Addis, har man ingen klausuler. Nei, i tillegg økes bistanden til landet opptil 600 millioner kr. Fra 2005 har antall historier om fengsel, overgrep, tortur og forsvinninger stadig økende. De siste to årene har det meste av media og menneskerettighetsorganisasjoner blitt kneblet. Dette parallelt med fengsling av journalister, opposisjonelle og flytting på store menneskegrupper. Overgrepene mot Oromo folket er svært brutale. Når etiopere lemlestes på åpen gate i Suadi Arabia, samtykker den etiopiske regjering. Når Yiligal Getnet er invitert til norsk Ud og RIA sin demonstrasjon blir han satt i husarrest. For lengst burde norske myndighter stoppet returavtalen, redusert bistandsstøtten og ryddte opp i de lengeventendes situasjon.

RIA har vært pådriver for at den manglende humanismen prøves for norsk rett, men rettsystemet har avvist gruppesøksmålet. Derfor har saken nå gått til Menneskerettighetsdomstolen i Strasbourg. De har åpnet sak mot Norge og sendt ti av sakene i retur til Norge som stikkprøver på de norske vurderingene. Vi håper på en uttalelse/dom fra Strasbourg før jul.

Det er ikke Norge verdig at vi har et lovverk som gir hjemmel for å behandle lengeventende på denne traumatiske måten. Det hjelper ikke med nye tater fra regjeringen om lovverket forblir uendret. Det burde i tillegg ikke være nødvendig å gå til sak mot vårt eget fedreland i saker hvor barn og voksne har hatt en uavklart situasjon i 5-18 år. Her står kampen. RIA har som mål å redde alle 500. Det gjenstår nå 331. Vi har ikke råd til å miste en eneste en.

Continue reading

Aside | Posted on by | Leave a comment

ታላቅ ሀገራዊ የተቃውሞ ጥሪ! ከወገኖቻችን ጐን በመቆም ብሄራዊ ክብራችንን እናስመልሳለን

 

ታላቅ ሀገራዊ የተቃውሞ ጥሪ!

ከወገኖቻችን ጐን በመቆም ብሄራዊ ክብራችንን እናስመልሳለን

ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈፀመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በመሆኑም በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ለማስቆምና የዜጐችን ህይወት ለመታደግ እንዲሁም ዜጐቻችን በአፋጣኝ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ መንግሥት እንዲያመቻች እና በተጨማሪም በዜጐቻችን ላይ ለደረሰው የአካል መጉደል፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈርና የህይወት መጥፋት ኃላፊነቱን የሚወስዱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ፤ ለተጐዱ ወገኖቻችንና ቤተሰቦቻቸውም አስፈላጊው ካሳ እንዲደረግላቸው ፓርቲያችን አበክሮ እያሳሰበ፤ የብሄራዊ ክብርና የወገኖች ስቃይ የሚያሳስባቸው አካላት በሙሉ በዚህ ታላቅ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የተቃውሞ እንቅስቃሴ አፈፃፀም፡-
1. በዜጐቻችን ላይ የአካል መጉደል፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈርና የህይወት መጥፋት ያደረሰው የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ኢምባሲ በሚገኝበት ቦታ አርብ ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ጀምሮ የሚደረግ የተቃውሞ ሰልፍ፣
2. ከአርብ ጠዋት ጀምሮ እስከ እሁድ ማታ ድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሀዘን ልብስ (ጥቁር ልብስ) በመልበስ በግፍ ለሞቱና ለተንገላቱ ወገኖቻችን ሀዘናችንን መግለፅ፣
3. የእምነት ተቋማት አርብ በመስጊድ በጁምአ ሥነ ሥርዓት ላይ እና ቅዳሜና እሁድ በአብያተ ክርስቲያናት የፀሎት ሥነ ሥርዓቶች ላይ ወገኖቻችንን በፀሎት እንዲታሰቡ፣
4. ቅዳሜ በሚደረገው የኢትዮጵያና የናይጄሪያ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ተጫዋቾቻችን ጥቁር ሪቫን በክንዶቻቸው ላይ አጥልቀው እንዲጫወቱ፣ እንዲሁም መላው ደጋፊ ጥቁር ጨርቆችን በመያዝ ወይም ልብስ በመልበስ ሀዘኑንና ቁጭቱን እንዲገልፅ፣

በፓርቲው የተወሰነ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ሲቪክ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዓለም አቅፍ ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ መላው ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጠራነው የተቃውሞ ሰልፍና እንቅስቃሴዎች ላይ በመገኘት ከግፉአን ወገኖቻችን ጐን መቆሙን እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
የወገኖቻችን ሰቆቃ እስኪያበቃ በፅናት እንታገላለን!!!

Posted in Uncategorized | Leave a comment

 

እንደ ሰው አንድ የሚያደርገን ባሕርይ፣ እንደ ኢትዮጵያዊነትም ሁላችንንም የሚመለከተንና የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት የማይነጣጥለው በደል በሳዑዲ አረብያ ግዛት እየተፈጸመ ነው። የጥቃት ዒላማዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የጥቃቱ ልክ የለሽነትና አሰቃቂነት ደግሞ ይበልጥ የጎላው በሴት እህቶቻችን ላይ ነው። ይህ ዛሬ በሳዑዲ አረብያ የሚደረገው ጥቃትን ማስቆምና ቁጣችን መቆምያ እንደማይኖረው ማሳየት ለነርሱ ብቻ ሳይሆን ለራሳችን ደህንነትም ጭምር የምናደርገው ነው። ምክንያቱም ነገ ተመሳሳይ ጥቃትና በደል በመላው አለም ይስፋፋል። በአፍሪካ ሀገሮች የተበተኑ ኢትዮጵያን ከሶማሌና ኤርትራ ከሚሰደዱት በተለየ ይዘረፋሉ፣ ይደፈራሉ ይዋረዳሉ። እንደ አገር ልጅ አብረው እንዳይቆሙ በዘር በሀይማኖትና በፖለቲካ አቋም ምክንየት የተበተኑ ናቸው። ለሰላሳና አርባ አመት አምባገነኖች ያደረጉት ጭፈጨፋና በደል ፍርሃትን ሰማይ ጥግ አውጥቶታል። እናም ኢትዮጵያዊ በየተበተነበት ሁሉ ተኛ ሲሉት የሚተኛ አውልቅ ሲሉት እርቃኑን የሚቆም ፈሪ እንዲሆን ተደርጓል። ሲቸግረው የሚጮኸውን ያህል ሲመቸው ለወገን የሚደርሰው ጥቂቱ ነው። ይህ ሊቀጥል አይገባም!Protest at Saudi Arabia Mission to United Nations!

ቀደም ባለው ጊዜ አንድ ኢትዮጵያዊ ጥቃት ቢደርስበት ባገኘው መሳርያ ዘነጣጥሎም ቢሆን ይገድል ስለነበር ማንም አይደፍረውም ነበር። በዘመነ ኮሎኒያሊዝም ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ሁሉ አንገት የማይደፉና ክብራቸውን የማያስነኩ ነበሩ። ዛሬ ጠቁመው የሚያስይዙ፣ ወገናቸውን የሚያሻሽጡና የሚሰልሉት ሁሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የዚህ ጽሁፍ መነሻም ሆነ መድረሻው የድሮውን አሁን እየሆነ ካለው ጋር ማወዳደር አይደለም። ለዚህ የሚሆን የቅንጦት ጊዜም የለንም። ዓላማው አሁን እየደረሰብን ያለውን በደል በቁርጠኛነት አንታገለው ነው። ይህ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ከዳር እስከዳር ማስነሳት ካልቻለና ቁጣቸውንም ለመላው አለም ማሳየት ካልቻለ እውነትም አገራችን እያበቃላት ነው ማለት ይቻላል።

የዱር አውሬ እንኳን ከዚህ የተሻለ ክብር አለው። እነዚህ አጅግ ሁዋላ ቀር የሆኑ አረመኔዎች ከእንስሳ እንኳን አንሰው አንዲት በፍርሃት ነብሷን የሳተችን ሴት አስር ሆነው የሚደፍሩትን እያየን የተደፈሩት ህጋዊ ናቸው ህገወጥ የሚል የሕግ አንቀጽ መረጣ ውስጥ ልንገባስ እንዴት ይቻለናል? በመላው አለም ያለ የሳዑዲ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ ሊደረግና የሳዑዲ ወሮበሎች በወጣት ሴቶች ላይ እያደረሱ ያለው ግፍ በመረጃም ተደገፎ በበራሪ ወረቀትም ተዘጋጅቶ ለአለም ሕዝብ ሊበተን ይገባዋል። ተፈጥሮ ዘይትን ስትቸራቸው አእምሮ ግን እንደነፈገቻቸው ከዚህ በላይ መረጃስ ከየት ይመጣል?

እንደ ትውስታ ከወሰድነው በኬንያ ያሉ ስደተኞች ላይ በደል ይደርስ በነበረበት ወቅት ያ በጨካኝነቱ የሚታወቀው መንግሥሰቱ ሀይለማርያም አንኳን “ኢትዮጵያውያኑ የተሰደዱት የምናራምደውን ፖለቲካ እንጂ ሀገራቸውን ጠልተው አይደለም…” በሚል ኬንያን ማስጠንቀቁን መስማቴ ትዝ ይለኛል። በየወሩ 40 ሺህ ሴቶችን እንልካለን እያለ እንደ እንቁላል በየአረብ ቤቱ ሲያከፋፍል የነበረው መንግስት ዛሬ ዜጎቹ እንዳይሆን መጫወቻ ሲሆኑ ዝም ብሎ መመልከቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው። ኢትዮጵያውያኑ ምናልባትም ኤምባሲውን ራሱን መቆጣጠር የሚገባቸው እስኪመስል ያስቆጣል።

በኢትዮጵያዊነት ላይ የተነጣጠረን ክፋት እንደ ሀገርና እንደ ሕዝብ ካላስቆምነው በሳዑዲ የተጀመረው መረን የጥላቻ ሰደድ ሊቀጣጥል የሚችልና የየሀገሩ የፖለቲካ ኪሳራ ማስተንፈሻ የሚሆነው አገር አጥቶ የተሰደደው ኢትዮጵያዊው ላይ ሁሉ ይሆናል። ይህንን በአስቸኳይ ለመቃወም ያሉ የትግል መንገዶች ሁሉ ክፍት ሊሆኑ ይገባል። እኔ አዘጋጀሁ እኔ ጠራሁ የሚል ደካማ የፖለቲካ ትርፍ ፍለጋ መንቀሳቀስ ሳይሆን ለሰብዓዊ ክብርና የመከራ ማጥ ውስጥ ሆነው የወገን ያለህ ለሚሉት እህት ወንድሞቻችን የድረሱልን ጥሪ ምላሽ እንስጥ። በጣም የሚያሳዝነው አብዛኞቹ ለስራ የሚሄዱት ወጣቶች የትምህርት ደረጃቸው አነስተኛ የሆነና በድህነት ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት የሆነው ይሁን ብለው ከቤታቸው የወጡ ናቸው። አንዳንዶቹም ግሩም እድል አንደሚገጥማቸው በደላላዎች እየተነገራቸው ከቤት ወጥተው የቀሩ ናቸው። ለኒህ አጋር መሆን ለሀገር እንኳን ደንታ ባይኖረን ለነብስ የሚበጅ ስራ ነው። የኢትዮጵያ ኮሙኒቲዎች፣ በኢትዮጵያ ስም የተቋቋሙ የሀይማኖት ማዕከላት፣ ሲቪክ የፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉ ለዚህ ዓላማ ቢቻል አደራጆች ካልተቻለም ዋንኛ ተሳታፊዎች ሊሆኑ ይገባል። ይህ በደል እጅ ለእጅ ሊያስተሳስረንና አንድ ላይ እንድንቆም ሊያደርገን የሚችል የጋራ ጉዳይ ነው። ዛሬ ነገ ሳንል በተደራጀና አለም አቀፍ ትኩረት ሊኖረው በሚያስችል አቅሙ እንነሳ ለወገንም አንድረስ።የመከራ ቀናችንን ለማሳጠር እንደ ሕዝብም ከአንገታችን ቀና እንድንል በያለንበት እንትጋ!

Aside | Posted on by | Leave a comment
 •  
  ዜጋህ እንደ ወንጀለኛ በየመንገዱ እየታፈሰ ሲታሰር፣ ምክንያቱ በግልጽ ባልታወቀ ሁኔታ ደግሞ አንዱ የአገርህ ልጅ በአረብ ፖሊስ ጥይት ተመትቶ ዋዕዩ በሚነድደው አስፓልት ላይ ደሙ ረግቶ ስትመለከት ምን ይሰማኻል? ይህ ሁሉ በሳዑዲ ምድር ላይ በየቀኑ እተፈጸመ መሆኑን ስትረዳ ውስጥህ ምን ይልኻል? ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከሌላ ዜግነት በቅጡ አንሶ ይሆን?ትናንት ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችባቸው 5 ዓመታት ብዙ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎችን አድርሳለች። ከነዚህ መካከል በግራዚያኒ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ የደረሰው የየካቲት 12 ጭፍጨፋ አንዱ ነው። በአዲስ አበባ በግፍ የተጨፈጨፉት የየካቲት 12 ሰማዕታት በሚዘከሩባቸው ቀናት አንድም ፈረንጅ በአዲስ አበባ መንገድ ዝር አይልም ነበር አሉ። ኢትዮጵያውያን በቁጭት ስለሚወጡ። እንኳን ጣሊያን እና የጣሊያን ዝርያ ያለው ቀርቶ ሌላ ፈረንጅም ቢሆን ይፈራ ነበር። ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ጥቃት ይኼን ያህል ቁጭት ነበራቸው።

  ዛሬ ኢትዮጵያን ወገኖቻችን በአረቦች እንደ ውሻ በየመንገዱ የሚደበድቧቸው በዚያን ዘመን ቢሆን ኖሮ አንድም አረብ በአዲስ አበባ ጎዳና በሰላም ይኼድ ነበር? ኢትዮጵያዊነት እንዲህ የረከሰውና የተዋረደው ድሆች ስለሆንን ብቻ ነው? ስንት ድሃ አገር ሞልቶ የለምን? ምነው እንደዚህ አልተንቋሸሹ?
  ኢትዮጵያዊውን “አለኹልህ” የሚለው ማነው? ውስጤ ሐዘን ሳይሆን ንዴት፣ ቁጭት፣ እልህ ነው ያለው። ካልተንገበገብን ታዲያ ምን ዋጋ አለን?
  አንድ ታሪክ የመጽሐፍ ቅዱስ አስታወሰኝ። ታሪኩ የብርሃነ ዓለም የቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ ነው። ይህ በእግዚአብሔር ተዓምር፣ በመባርቀት የተጠራ ሐዋርያ ታሪክ ነው። ቅ/ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በሚያስተምርበት ጊዜ ትምህር…

Aside | Posted on by | Leave a comment

Posted under

ዜና

Comments

Leave a Comment

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ እና የፕራይቬታይዜሺን ኤጀንሲ በፖለቲካ ጫና ስራውን በአግባቡ እየተወጣሁ አይደለም አለ፡፡

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የልማት ኤጀንሲው የስራ ሃላፊ ለዘጋቢያችን እንደነገሩት ድርጅቱ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት የተለያዩ የመንግስት ይዞታ የነበሩ ተቋማት በጥናት ለህዝብ ጥቅም የመሸጥ የመለወጥ ፤ ስልጣን ተሰጥትቶታል፡፡ ይህን ስራ ተግባራዊ ለማድረግ አዳጋች ሁኖብኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እስካሁንም የአዋሺ አግሮ ኢንዱስትሪ ቲብላ እርሻ፣ የመካከለኛ አዋሺ የእርሻ ልማት፣  በሰሜን ኦሞ እርሻ ልማት ውስጥ የሚገኘው ኦሞራቴ እርሻ ልማት በመንግስት አመራሮች ጫና በብዙ ሚሊየን ብር ኪሳራ ወደ ግል ተዛውሯል፡፡

በባለሃብቶች እጅ ባሉ ባለስልጣኖች ምክር የሚመነዘሩት የባለሃብቶች እና የባለስልጣናት ትስስር ለሰፊው የህዝብ ጥቅም ሳይሆን የመንግስት ባለስልጣናትን ኪስ የሚያደልቡ አሰራሮች መጠቀሚያ እንደሆነ ነው ያመለከቱት ፡፡

ካሁን በፊትም ፤ የአዋሺ አግሮ ኢንዱስትሪ ቲብላ እርሻ ወደ ግል የተዛወረበት መንገድ ግልጽነት የጎደለው ስምምነት ነበር ፡፡

የመካከለኛ አዋሺ የእርሻ ልማት በሊዝ ተሺጦ ያለ አግባብ በሚልየኖች የሚቆጠር ብር በአየር ላይ ባክኖ ቀርቱዋል፡፡ በዚህም  ከ98 በላይ ቤተሰብ አሰተዳዳሪ ሰራተኛች ያለ የስራ ዋስትና ተብትነዋል፡፡

በሰሜን ኦሞ እርሻ ልማት ውስጥ የሚገኘው የሚገኘው ሞራቴ እርሻ ልማት ያለበቂ ተመን ከተሸጡት ድርጅት መካከል ቀዳሚው ነው፡፡ በስጦታ እንደ ተላለፈ የሚቆጠረው ይህ  የኮሪያ ባለሃብቶች የልማት ፕሮጀክት ወደ ግለሰቦች ሲዛወር ከህግ እና አሰራር ቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ነው በማለት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡

ለልማቱ የተገዙትን መኪናዎች ጨምሮ  ከመሳሪያዎች ጋር ከ32 ሚልየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ባለበት ሁኔታ፣ ከገበያ ዋጋ በታች በሆነ ሁኔታ ለሺያጭ ውሎዋል፡፡

ኤጅንሲው የመንግስት ልማት ድርጅቶችን መቆጣጠር በአግባቡ የመስራት አቅሙን ያዳከመው የኢህአዴግ መንግስት ፣  ሸበሌ ትራንስፖርት  ኮምቦልቻ ፤ ወይራን የመሳሰሉ ድርጅቶች  ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተላልፈው እንዲሰጡ  ከባለስልጣናት በቃል በተላለፈ ትእዛዝ ያለማንም መስረጃ ለሶስተኛ ወገን ተላልፈው ተሰጥተዋል።

የሸበሌ ማዴአዎች  ለሌላ ሶስተኛ ወገን ሲተላለፉ ከ 397 በላይ ተቀጣሪዎች ያለ ስራ ካሳ ወይም ምትክ የስራ ዋስትና ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡

የየረር የዱቄት ፋብሪካ ተዘግቶ 41 ሰራተኛች ተፈናቅለው የስራ ዋስትና አጥተዋል፡፡ የሰራተኞች መብት እና ጥቅም እንዲሁም ውለታቸውን ባላከበረ ሁኔታ ተላልፈው ተሺጠዋል፡፡ የመንግስት ሃብቶች ወደ ግል ሲዛወሩ የሰራተኞችን መብት ባከበረ እና የስራ ዋስትናቸውን በተጠበቀ መካሄድ አለበት ቢልም ህጉ  ሳይተገበር ቀርቱዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካቶች  በቁሳዊ እና የማህበራዊ ኪሳራ እንዲኖሩ መገደዳቸውን እና ልጆቻቸውን ለማስተማር እና  በልቶ ለማደር አቅም እንዳጠራቸው ለዘጋቢያችን ግልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት ኤጀንሲው ወደ ግል እንዲዛወሩ በ ንግድ ማተሚያ ቤት፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ ግብርና ሜካናይዜሽንና ግዮን ሆቴል ጨረታ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ከሁለት ወራት በፊት በወጣው ጨረታ ከእነዚህ ኩባንያዎች ጋር ሌሎች ሦስት የመንግስት የልማት ድርጅቶችም የባሌና የአርሲ እርሻ ልማት ድርጅቶች፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎችና ቡና ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ኢንስቲትዩት ለሽያጭ መቅረባቸው ይታወቃል፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴር ጨረታቸውን አየር ላይ እንዳለ እንዲቋረጥ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ሦስቱ ድርጅቶች እንዳይሸጡ በመወሰኑ ከጨረታ ሒደቱ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ሁለቱ ማለትም ባሌና አርሲ የእርሻ ልማት ድርጅቶች ለኦሮሚያ ምርጥ ዘር ድርጅት፣ እንዲሁም የኮንስትራክሽንና ቡና ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ኢንስቲትዩት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሸን እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡

በ2004/5 በጀት አመት ጊዮን ሆቴል፣ አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ፣ ቡና ቴክኖሎጂና ምህንድስና እንዲሁም የኢትዮጵያ ማእድን አክሲዮን ማህበር ወደ ግል የዛወራሉ ቢባልም ሳይሸጡ ቀርተዋል።

ቢሊቶ እርሻ ልማት፣ ሀማሬሳ የምግብ ዘይት አክሲዮን ማህበርና አርባ ጉጉ እርሻ ልማት በአዲስ ለጨረታ ከሚቀርቡ ድርጅቶች ውስጥ ሲካተቱ ፥ በሰኔ ወር መጨረሻ ለጨረታ ከቀረቡት ውስጥ የባቱ ኮንስትራክሽን ጨረታ ተሰርዞ በሌላ የመንግስት ድርጅት ስር እንዲተዳደር በቦርዱ መወሰኑን በኤጀንሲው የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ይናገራሉ።

ወደ ግል ሳይዛወሩ በመንግሥት እጅ ይቆያሉ የተባሉትና ኤጀንሲው ስትራቴጂክ ካላቸው ተቋማት መካከል የጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጅት (ጅንአድ)፣  ሙገር ሲማንቶ ፋብሪካ፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ድርጅት (ኢትፍሩት) ይገኙበታል፡፡

የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ቀደም ሲል በእጁ ላይ 287 ኢንተርፕይዞች ነበሩት፡፡ እስከ 2004 ዓ.ም. ድረስ 236 ኢንተርፕራይዞችን ለግል ካዛወረ በኋላ፣ በአሁኑ ወቅት የቀሩት 51 የልማት ድርጅቶች ናቸው፡፡

ከእነዚህ ውስጥ ሃያዎቹን በ2005 ዓ.ም. ወደ ግል ለማዛወር  አውጥቷል፡፡ ኤጀንሲው የመንግሥትን ኢንተርፕራይዞች በሽያጭ ወደ ግል ማስተላለፍ በጀመረበት በ1987 ዓ.ም. አምስት ኢንተርፕራይዞችን ብቻ ነበር ወደ ግል ያዛወረው፡፡ በቀጣዩ ዓመት እስከዛሬ ድረስ ክብረወሰን ሆነው የተመዘገቡትን 127 ኢንተርፕራይዞች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሽያጭ አስተላልፏል፡፡

ከፍተኛ ሙስና እንደተፈጸመባቸው በተነገረው በዚህ ሽያጭ፣ ግብር ከፋዩ ክብረተሰብ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት ለዘረፋ ተጋልጧል።

esat

Aside | Posted on by | Leave a comment