የኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰለፍ በሃሽታ ከተማ

የኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰለፍ በሃሽታ ከተማ

ፖለቲካዊ ማናለብኝነት እንደ ሥርዓት
“ፍጹም ሥልጣን ፍጹም ያባልጋል” የሚለውን አነጋገር ኢትዮጵያውያን በተግባር እናውቀዋለን። ዴሞክርሲን የተመኘነውም የመንግሥት ሥልጣን የሚይዙ ቡድኖች እና ደጋፊዎቻቸው መባለጋቸው ባይቀርም ፍጹም እንዳይባልጉብን ያደርግልናል ብለን እንደሆነ የታወቀ ነው። ዴሞክራሲ ይህን ማረጋገጥ ከሚችልበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት ከዚያ ብልግና ሊታደገን እንደማይችል በዚህ ምርጫ ታዝበናል።
ኢሕአዴግና የተወሰኑ አባሎቱ ከምርጫው በፊትም ሆነ በኋላ የሚያሳዩት ማናለብኝነት ለደጋፊዎቻቸው ጭምር አሳፋሪና አስጊ ነው።የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ከምርጫው በፊት በፓርላማ ቀርበው “ከምርጫው በኋላ እናስራችኋለን” እያሉ የሚያስፈራሩት፤ የአሁኑ ደግሞ “ምህረታች ገደብ ስለሌለው አናስራችሁም አትፍሩ” እያሉ የሚናገሩት ተተኪዎቻቸው የፍጹም ሥልጣን ባለቤትነት በእጃቸው ስለገባ ብቻ ነው። ስለዚህም ፍጹም ለመባለግ የሚያስችለው ነገር ሁሉ ለእርሳቸውና ለፓርቲያቸው ተመቻችቷል። አንድ መጥፎ ምልክት “ሁሉም ነገር የኢሕአዴግ እና ለኢሕአዴግ ብቻ” የሚለው ነው።
የምርጫው ተሞክሮ ለኢሕአዴግ የሚያስተላልፈው ተሞክሮ የተለያየ ነው። ለአቶ ሃይለማርያም ና ለፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ምናልባት ተመሳሳይ በስም ዴሞክራሲያዊ የሚመስሉ በተግባር ግን ያለምንም ጥርጥር የእነርሱን አሸናፊነት የሚያረጋግጡ ተመሳሳይ የ“ምርጫ ድራማዎች” እየሠሩ ለረጅም ጊዜ ሥልጣን ላይ መቆየት እንደሚቻል ይሰማቸው ይሆናል። በእነዚህ ድራማዎች ተቃዋሚ ነኝ ለሚለው “የማይጠፋበት ግን የማያሻንፍበት፤ የሚኖርበት ነገር ግን የማይጠናከርበትን” መድረክ እየፈጠሩ የድራማው ዘላቂ ተዋናይ ማድረግ እንደሚቻል የባለፈው ተሞክሮ አስተምሯቸው ይሆናል…

Advertisements
Image | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s