1. ደ ሻማ እየቀለጡ ለሚያበሩልን በሙሉ…

    ሰሞኑን ገቢዎች ሚኒስተር ለሆነ ጉዳይ ስመላለስ፣ ጉዳዬን የያዘችውን ልጅ ተራዬ ደርሶ እስከማነጋግራት ዝም ብዬ ውሎዋን አስተውል ነበር። ከፊቷ የተደረደሩትን ባለጉዳዮች ፣ ግማሹን የቀረ መረጃ እንዲያመጣ ስትመልስ፣ ግማሹን እሷ ጋር ሳይሆን ሌላ መስኮት ጋር መሄድ እንዳለባት ስታስረዳ፣ የቀረውን ደግሞ ለመጣበት ጉዳይ ስታስተናግድ፣ ቀኗ አልቆ ሌላ ቀን ይጀምራል። የስራዋን ድግግሞሽነት፣ አሰልቺነት እና አድካሚነት ሳስበው በጣም አደነቅኳት፣ ለዚያውም ለማይረባ ደምወዝ! እኔንም በጸባይ ስታስተናግደኝ ቆይታ ለሶስተኛ ቀን ሳገኛት፣ ለአራተኛ ቀን ተመልሼ እንዳልደክም በማሰብ ሰልኬን ተቀብላ፣ ከዛም… አስታውሳ ደውላ፣ ጉዳዬ ሲያልቅ አሳወቀችኝ። ከዛ ሁሉ ስራ መሀል እኔን አስባ በመደወሏ ለቅን ልቧ ከልብ አመሰገንኳት።

    ታድያ ይህቺ ስሟን እንኳ ያለወቅኩት ልጅ፣ እኔ ሁለት ቀን ብሰራው መሞት የሚያምረኝን ስራ ሕይወታቸውን በሙሉ ሲሰሩ የሚኖሮ ሰዎችን አሳሰበችኝ። በየመንግስት መስሪያ ቤቱ፣ በየመስኮቱ ህዝብ ሲያገለግሉ የሚውሉትን ሰራተኞች፣ ቄራ ተቀጥረው የሚሰሩትን በሬ አራጆች፣ ለመንገድ እና ለቤት ግንባታ በጉልበት ስራ የሚያገለግሉትን ድንጋይ ፈላጮች፣ የአንድ ቤተሰብ የወር ልብስ በ70 ብር ተቀጥረው ሲያጥቡ የሚውሉትን ተመላላሽ ልብስ አጣቢዎች፣ በየቢሮው እና በየትምህርት ቤቱ ጠዋት ስንገባ፣ ትናንት ስናቦካ የዋልነውን ጽድት አድርገው የሚጠብቁንን ጽዳት ሰራተኞች፣ በጥቅሉ፣ እነሱ ሳያልፍላቸው የኛን ህይወት የሚያቀሉልንን ሰዎች በሙሉ አስታወስኳቸው። ታላቅ ክብር፣ አድናቆት እና ምስጋና እንደ ሻማ እየቀለጡ ለሚያበሩልን እህት እና ወንድሞቻችን!

    Like · · Share · Thursday at 9:52am ·

    Like · · Unfollow Post · 18 hours agoSee More

     
Advertisements
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s