ሦስት ዓይነት ኢትዮጵያዊያን

1. መግቢያ

Imageምን ነካን? ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ምን ብናድርግ ይበጀናል? ይህ ጽሁፍ እነዚህ ጥያቄዎች የፈጠሩብኝ ስጋት

በፋሽስት ጣልያን አምስት ዓመታት የወረራ ዘመን በአገራችን የተፈፀሙ አሳዛኝ ክስተቶች አሁን በወያኔ አገዛዝ
እየተደገሙ ነው። ያኔ ሦስት ዓይነት ኢትዮጵያዊያን ነበሩ፤ ዛሬም ሦስት ዓይነት ኢትዮጵያዊያን አሉ። እነዚህ ሦስት
ዓይነት ኢትዮጵያዊያን ከመጠሪያቸው በስተቀር ባህሪያቸው ተመሳሳይ ነው።

በፋሽስት የወረራ ዘመን ተስማምቶ፣ ተመሳሰሎ፣ ተለሳልሶ፣ ተሞዳምዶ መኖር ተበረታታ። በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ደግሞ
ይህ የአኗኗር ስልት “ልማታዊ” እየተባለ ይሞካሽ ጀመር፤ ሕዝቡ ግን “ወይን ለመኖር” ብሎ ጠራው። ወይን ለመኖር
በከፍተኛ ፍጥነት በመስፋፋቱ ጭቆናንና ጥቃትን እየታገሰ የሚኖር ከፍተኛ መጠን ያለው የኅብረተሰብ ክፍል
እየተፈጠረ ነው። ይህ አጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።

ይገልጽልኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። በቂ ባይሆንም ችግሩን መቀነሻ አንድ መንገድ ለማመላከት እሞክራለሁ።
2. ኢትዮጵያዊያን በጣልያን ወረራ ዘመን
በኢትዮጵያ ምድር የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተረግጦ የፋሺስት ጣልያን ባንዲራ ከፍ ብሎ የተውለበለቡባቸው አምስት
የመከራና የተጋድሎ ዓመታትን (1928 – 1933) እናስታውስ። በዚያ ጊዜ ሦስት ዓይነት ኢትዮጵያውያን ነበሩ።
2.1. አርበኞች እነዚህ ጠላት በድርጅት፣ በትጥቅና ስንቅ እንደሚበልጣቸው እያወቁም ቢሆን በአልበገር
ባይነት ሲፋለሙ የቆሙ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ናቸው። የእነዚህን ወገኖቻችን ተግባር በክብርና በወኔ እናስታውሳለን። “አባቶቻችንና እናቶቻችን” ወይም “ቀደምቶቻችን” ብለን
ስንናገር በአብዛኛው በአዕምሮዓችን የሚመጡት እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ያኔ
ቁጥራቸው ጥቂት የነበረ ቢሆንም እንኳን ፋሽስት ጣልያን ተረጋግቶ “መንግሥት”
እንዳይሆን አድርገውታል። ከድል በኋላ ብዙዎቹ በግል የተረሱ ቢሆንም ያኔ እነሱ የነበሩ
በመሆናቸው ነው የዛሬው ትውልድ ስለ ቀድሞው የአርነት ተጋድሎ ታሪክ ደረቱን ነፍቶ
ለመናገር የሚደፍረው። እነሱ በመኖራቸው ነው እኔም “የቅኝ ግዛት ዘመን” ሳይሆን “የወረራ
ዘመን” ብዬ ስለዚያን ጊዜ የምጽፈው።  ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s