ሃና ወልደማርያም

 •  
  ሀና ውልይም

  ሀና ውልያም ከኢትዮጵያ በ Larry P. Williams and Carri D. Williams እና 7 ልጆቻቸውን ለመቀላቀል በአሜሪካ ሲያትል በሚባል ከተማ በ2008 ዓ/ም ገባች :: ሀና ከኢትዮጵያ ሰትመጣ የተሻለ ኑሮና ትምህርት እንደሚኖራት ቢመሰልም ያጋጠማት ግን ማንም የሰው ልጅ ይደረግበታል ተብሎ የማይታሰብም ነበር ::

  እነዚህ ግለሰቦች ሀናን በማሰራብ ፣ በመደብደብና እንዲሁም የከብት በረት ውሰጥ በማሰተኛት ሲቀጥዋት ከቆዩ በኋላ በመጨረሻም ከፍተኛ ብርድና ዝናብ በነበረነት ቀን እራቃነ… ሰጋዋን ውጪ እንድታድር አድርገዋት ነበር :: ያቺም ቀን በርሃብና በዱላ የተጎዳው የሀና ሰውነት ብርድ ዝናብ ሲወርድበት አደረ በማግሰቱም ሀና ጭቃ ላይ በፊቷ ተደፍታ ተገኝታለች:: መርማሪዋቹ እንዳሉት ሰውነቷ በኤሌትሪክ ገመድ የተገረፈበት ምልክት ይታይበታል ጭንቅላቷላይም ትልቅ እብጠት ነበረው በዛላይ ሰውነቷ በጣም የከሳ እንደነበር ገልፀዋል:: ሀና ሽንት ቤት የምትጠቀመው ከሁሉም ተለይታና ከቤት ወጣ የለ ነበር ይህንንም ለምን እንደሆነ ሲገልፁት የጉባት በሽታ (hepatitis) ሰለነበራት እኛ ላይ እንደይጋባ ብለን ነው ሲሉ ገልፀዋል :: የሀና እድሜ እንኳን በትክክል የሚያውቅ የለም ከ 13 እሰከ 16 ትሆናለች ተብሎ በግምት ሲነገርም ተሰምቷል የዚህም ምክንያት Adaption Agency የውሽት ወረቀት በማዘጋጀቱ ነው ብለዋል ::ይህም እውነተኛ ነገር ነው እነዚህ ልጆች ከሀገር ሲወጡ ወላጆቻቸው ሞተዋል፣ አሳዳጊ ካላገኙ ሴተኛ አዳሪ ይሆናሉ፣ እድሜ ይቀነሳል ለወላጅ ደግሞ ዶክተርና ሳይንቲሰት ይሆናሉ እንጂ ይገደላሉ ይራባሉ ኩላሊታቸው ይሽጣል ብለው ሲናገሩ አይሰማም ::

  ይህ በሀና የተፈፀመው አሰቃቂ ድርጊት በብዙ ልጆች ላይ ሊፈፀም እንደሚችል አልጠራጠርም :: ይህ በተሰማ በወሩ የዚህ አይነት ድርጊት በሌላም ሁልት ኢትዮጵያዊያኖች ላይ ተከሰቶ ነበር ነገር ግን ሁለቱም ልጆች የአካል ጉዳት ቢደርሰባቸውም በህይወት ተርፈዋል::

  እኛ ኢትዮጵያኖች ፍቅር የምናውቅ፣ ሩሩህ፣ አዛኝ፣ ያለንን ተካፍለን የምናድር ፣ የሌላወን ልጅ ከራሳችን ለይተን የማናይ፣ የርስ በራሳችን ጠባቂ፣ ነበርን ::ምነው ዛሬ ልጆቻችን ሲሸጡ አብረን አሻሻጭ ሆንን :: አንድ በዚህ መልክ የወጣች ወጣት ” ተሸጥኩኝ” ነው ያምትለው ይህ በጣም ያሳዝናል :: ታዲያ በዚህ መልክ እያወጡ ያሉት ልጆች ወደፊት ምን ይሉን ይሆን ? እኛሰ ተጠያቂ አንሆንም ? ብዙ ልብ ያሚሰብሩ አሳዛኝ ታሪኮችን እንሰማለን ያው ከንፈር መጠን እናልፈዋለን

  በመጨረሻም…. ሲያትል ያላቹ ወገኖቼ …. እነዚህ የሀና ገዳዮች ሰሞኑን ለክስ ቀርበዋልና እባካቹ ፍርድ ቤት በመሄድ ሀናም ወገን እንዳላት አሳዩልን :: እግዚያብሔር የሰጣትን ሕይወት የነጠቋት እነዚህን ነፍስ ገዳዮችን የሚገባቸውን ፍርድ እንዲያገኙ በማንኛውም መንገድ እንረዳዳ ::

  እግዚያብሄር የሀናን ነፍስ በገነት ያኑርለን !!

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s