አቶ ግርማ ወልደሰንበት አረፉ::

የአንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ታጋይ የነበሩት አቶ ግርማ ወልደሰንበት አረፉ::

Image

አቶ ግርማ ወ/ሰንበት በ1984 ዓ.ም. መዐህድን በመመስረት፣ ህይወታቸው እስካለፈበት ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ደግሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) የብሄራዊ ም/ቤት አመራር አባል በመሆን ታግለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፓርቲያችን አንድነት ከፍተኛ አመራር ሰጭ በመሆን ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የኢትዮጵያን ህዝብ የነፃነትና የዴሞክራሲ ጥያቄን ለማሳካት ግንባር ቀደም አርበኛ በመሆን ሲታገሉ የቆዩ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ናቸው፡፡አንድነት ፓርቲ በቁርጥ ሰዓት ጀግናውን ኢትዮጵያ ልጅን በማጣቱ ታላቅ ሐዘን ተሰምቶታል፡፡

የአቶ ግርማ ወ/ሰንበት የቀብር ስነስርዓት ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቀኑ 6 ሰዓት በሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን ስለሚፈፀም የአንድነት ፓርቲ አባላትም በስፍራው በመገኘት በክብር እንድንሸኛቸው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ፈጣሪ መፅናናቱን እንዲሰጣቸው እንመኛለን፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)
ብሔራዊ ምክር ቤት

Advertisements
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s