የዕለቱ ዋና ዋና ዜናዎች

—————–
1, አየር መንገድ በድሪምላይነር አውሮፕላን ሳቢያ ገቢው ቀንሷል
በድሪምላይነሮቹ ላይ አሁንም ጠንካራ እምነት አለኝ አለ- ለሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ አድርጓል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ በቅርቡ ከተረከባቸው ዘመናዊዎቹ አራት ድሪምላይነር አውሮፕላኖች መካከል በአንዱ ላይ በእንግሊዝ ለንደን አውሮፕላን ማረፊያ በቆመበት በደረሰበት ችግር ምክንያት፣ በአየር መንገዱ እንቅስቃሴና ገቢ ላይ ጉዳት ማድረሱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስታወቁ፡፡
2, ከብአዴን ድርጅቶች አንዱ የሆነውና በጥረት ሥር የሚገኘው ጣና ሞባይል ከስሮ ሠራተኞችን መቀነስ ጀመረ፡፡
ጣና ሞባይል የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ደንበኛ ከሆነው ከቻይናው ግዙፍ ቴሌኮም ኩባንያ ዜድ.ቲ.ኢ ጋር በጋራ ለመስራት በደረሱት ስምምነት መሰረት በ2003 ዓ.ም በ50 ሚሊየን ብር ወጪ በባህርዳር ከተማ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችን ማምረቻ ፋብሪካ በመክፈት ምርቱን ለአገር ውስጥ ገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡
ሆኖም ፋብሪካው ባልታወቀ ሁኔታ ከቀጠራቸው ሠራተኞቹ መካከል ወደ 70 የሚጠጉትን ከዚህ ወር መጀመሪያ ጀምሮ በይፋ ማሰናበቱን ምንጮቻችን ጠቅሰዋል፡፡
3, በደሴ ከተማ መንግስት የገደላቸውን ሼህ ኑሩን በማስመልከት ኢ.ቲ.ቪ ያሰራጨውን ዘጋቢ ድራማ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በግዳጅ እንዲመለከቱት እየተደረገ መሆኑ ተጠቆመ::
በደሴ ከተማ ከሳምንታት በፊት ጭለማን ተገን በማድረግ መንግስት ያስገደላቸውን የደሴ ከተማ የአህባሽ እምነት ፊት አውራሪ የነበሩትን ሼህ ኑሩን በማስመልከት መንግስታዊው የቴሌቪዥን ጣብያ ያሰራቸውን ዘጋቢ ድራማ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በግዳጅ እንዲመለከቱት እየተደረገ መሆኑንን ምንጮች አስታውቀዋል፡:
4, የሰቆጣ ከተማ ወጣቶች “ችግራችን በዝቷል ነጻነት እንፈልጋለን” አሉ
ባለፈው ቅዳሜ ከላሊበላ ሰቆጣ ይሰራል ተብሎ የነበረው መንገድ ባለመሰራቱ የተበሳጩት የከተማዋ ነዋሪዎች በራሳቸው አነሳሽነት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ወጣቶቹ አጋጣሚውን በመጠቀም ” ነጻነት እንፈልጋለን፣ እኛ ወታቶች ብዙ ችገሮች አሉብን፣ ሰቆጣ መብት የለም፣ ብልጭጭልታ የእድገት ምልክት አይደለም፣ እድገት የለም፣ መንገድ ላሳ ህዝብ መንገድ ሊከለከል አይገባውም፣ልማት በተግባር እንጅ በውሬ አይደለም፣ ዋግ ለጦርነት ብቻ ሳይሆን ለልማትም ዝግጁ ናት፣ ዋግ ውስጥ ለውጥ የለም፣ መንገዳችን ልንነጠቅ አይገባም፣ የህዝብ ድምጽ አይጣስም የሚሉትን እና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል፡፡
5, የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአፍሪካ ኅብረት) መሥራች ለሆኑት ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የመታሰቢያ ሐውልት እንዲቆምላቸው ተጠየቀ፡፡
ይህንን የጠየቁት የድርጅቱ/የኅብረቱ 50ኛ ዓመት ኢዮቤልዩ ክብረ በዓልን ለማክበርና መሥራቾች አባቶችን ለመዘከር ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደው ውይይት ላይ ከተገኙ ተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ነው፡፡
ከዛሬ ሃምሳ ዓመታት በፊት የድርጅቱ/ኅብረቱ መሥራች ስብሰባ በተካሄደበት አፍሪካ አዳራሽ ውስጥ በተከናወነው ውይይት ላይ የተገኙት እነዚሁ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት፣ ሐውልቱ መቆም ያለበት በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ፣ አለበለዚያም በደርግ ሥርዓት የሌኒን ሐውልት ቆሞበት በነበረው ሥፍራ ነው፡፡
ለሐውልቱም ግንባታ መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s