መንግስት ህዝቡን ማስፈራራቱን ቀጥሎበታል!!

 
በዛሬው ጁምዓ በአንዋር መስጂድ ምንም አይነት ተቃውሞ እንደማይደረግ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ከጁምዓ ሰላት በፊት በርካታ የፖሊስ መኪኖች በአንዋር መስጂድ ዙሪያ ከነሙሉ ትጥቃቸው ሲዟዟሩ የነበረ ሲሆን፤ የተወሰኑት መኪኖች ደግሞ በርካታ አስለቃሽ ጭስ የያዙ አድማ በታኞችንና የፌደራል ፖሊሶችን በአካባቢው እንዳራገፉ የ”ፈስቢር” ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

አንዋር መስጂድ የጁምዓን ሰላት ለመስገድ ይገቡ የነበሩ የተወሰኑ ሙስሊሞችም፤ ፖሊሶችን አስለቃሽ ጭስ ይዘው ሲያዩና፤ በብዛት በአካባቢው ሰፍረው ሲመለከቱ፤ መንግስት ህዝቡን ለመተንኮስ አስቦ እንደሆነ ስለገባቸው፤ እድሉን ለመንፈግ ብለው፤ ከአንዋር መስጂድ በመውጣት ወደ ሌሎች መስጂዶች ሄደው ጁምዓን መስገዳቸውንም ለማወቅ ችለናል፡፡

እኛ ሙስሊሞች ተቃውሞ ማድረግ ካለብን ፖሊሶች በጭራሽ ሊገቱን አይችሉም፡፡ እኛ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ማድረግ ባለብን ቀናት ሁሉ እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ሰላማዊ ህዝብን በመግድል፤ በመደብደብና በማሰር ጥያቄውን አስቀራለሁ ብሎ መንግስት ካሰበ ወላሂ ትሳስቷል፡፡ ሙስሊሙን ለማስፈራራት በየመስጂዱ የሚያደርገው የጦር መሳሪያና የፌደራል ፖሊሶች ሾው (show) እኛን በጭራሽ ወደ ኋላ እንድንል አያደርገንም!!

ድል ምንግዜም ለእውነተኞች ነው!! 

Advertisements
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s