ሰበር ዜና .የሀገር ውስጥ የደሀንነት መምሪያ ሃላፊ በቁጥጥር ስር ዋሉ ወደ እስር ቤትም ተወረወረ!!

የሃገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀልተጠርጥረው በቁጥር ስር ዋሉ።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋሉት የነበራቸውን ስልጣን ያለ አግባብ መጠቀም ፥ ምንጩ ያልታወቀሃብት በማፍራት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል  ተጠርጥረው ነው።

ከፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው  ፥ ተጠርጣሪውበፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።

ኮሚሽኑ ግለሰቡ ፈጽመውታል ከተባሉ የሙስና ተግባራት ጋር በተያያዘ ሌሎች ተያያዥምርመራዎችን እያካሄደ ይገኛል።

የዛሬ አመት ገደማ ኮሚሽኑ በአቶ ወልደስላሴ  ወንበር ላይ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ አቶ አይቼውተፈታን በተመሳሳይ

ወንጀል ከሷቸው በአሁን ጊዜ  ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው  ።

አቶ አይቼው ከገቢ በላይ ምንጩ ያልታቀ ሃብት አፍርተዋል የተባሉባቸው ሆቴሎች እና ሌሎችንብረቶች በአሁን

ጊዜ መታገዳቸው ይታወቃል።

ህወሓት በሁለት ቡድኖች መከፈሉ ይታወቃል። የደህንነት ሓላፊዎችም እንዲሁ በሁለት የተከፈሉ ናቸው። ሁለቱ የደህንነት ሓላፊዎች አቶ ጌታቸው አሰፋና አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ናቸው። በሁለቱም ከፍተኛ ጠብ አለ። አቶ ጌታቸው የነ አርከበ ቡድን ሲሆን አቶ ወልደስላሴ ግን የነ አባይ ወልዱ ሁኖ የወይዘሮ አዜብ መስፍን የቀኝ እጅ ነው።

ሁለቱም የደህንነት ተጠሪዎች በደም የሚፈላለጉ ናቸው። ባለፈው የህወሓት ጉባኤ አቶ ወልደስላሴ ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተጠቁሞ አቶ ጌታቸው ጠንከር ያለ ትችት በማቅረቡ ሳይሳካለት ቀርተዋል። መለስ በህይወት እያለ (በአዜብ ምክር መሰረት) አቶ ጌታቸውን በአቶ ወልደስላሴ ለመተካት አቅዶ ነበር (ሞት ቀደመው እንጂ)።

አቶ ጌታቸው ለመለስ ከማይታዘዙ የህወሓት መሪዎች አንዱና ዋነኛው ነው። ከመለስ ጋር በብዙ ነጥቦች ላይ አይስማሙም፤ የተባለውን ሁሉ የሚሰማ አይደለም። ጠንካራ ነው። ከሙስና የፀዳ የህወሓት ባለስልጣን አቶ ጌታቸው አሰፋ ነው።

የትግራይ ቡድን የአዲስ አበባውን ለማሸነፍ በመለስ ራእይ ስም ከህዝብ መነጠል ችላል። የአዲስ አበባው ደግሞ በሙስና ሰበብ የትግራይ ቡድኑን እያሰረ ይገኛል።

ዛሬ የኢህአዴጉ ሚድያ ‘ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት’ የሃገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነግሮናል። ጥሩ መጠላለፍ መሆኑ ነው። አቶ ወልደስላሴ የነ አቶ ገብረዋህድ ጓደኛ ነው። አቶ ወልደስላሴ ከታሰረ ወይዘሮ አዜብ መስፍንስ?

ለማንኛውም ቸር ያሰማን!

Advertisements
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s