ኢትዮጵያ ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ በምትጫወትበት ቀን… ሰማያዊ ፓርቲ የሰልፍ ፍቃድ ጠየቀ!! (“ጨዋታው እና ሰልፉ አይገናኝም” ተብለናል)

 

 (ኢ.ኤም.ኤፍ) – ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ፣ ነሃሴ 26 ቀን፣ 2005 ዓ.ም. ሊያካሂድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት ሃይሎች ጣልቃ ገብነት ለጊዜው የተጨናገፈ መሆኑ ይታወሳል። ሆኖም የፓርቲው መሪዎች እና አባላት ዳግም ሌላ ሰላማዊ ሰልፍ እሁድ ጳጉሜ 2፣ 2005 ለማድረግ እንዲችሉ ለመንግስት የፈቃድ ጥያቄ አቅርበዋል፤ መግለጫም አውጥተዋል። ነገር ግን አንድ የታዘብነው ነገር አለ። ቅዳሜ የኢትዮጵያ እና ሴንትራል አፍሪካ እግር ኳስ ጨዋታ ይካሄዳል። ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ኳስ ጨዋታው እና ሰልፉ ጠዋትና ከሰአት ስለሆነ፤ ችግር እንደማያመጣ ኢ.ኤም.ኤፍ ማስተካከያ እንዲያደርግ ተጠይቋል። ማስተካከያው እንዳለ ሆኖ፤ ቀደም ሲል ለህትመት የበቃውን ዜና ግን ለአንባብያን ግንዛቤ ያህል ሳንቆራርጥ እንደነበር ትተነዋል።

ይህ ወሳኝ ጨዋታ እንደመሆኑ መጠን፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚያደርገውን ጨዋታ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ይከታተሉታል። በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መስቀል አደባባይ ተገኝተው ጨዋታውን በስክሪን ያያሉ። ሰማያዊ ፓርቲም ሰላማዊ ሰልፉን የጠራው በዚሁ በመስቀል አደባባይ ነው። መንግስት ፈቃድ መስጠቱን ቢከለክል፤ እዚያ ከተሰበሰበው ህዝብ ጋር በተቀላቀል ሊያከብረው ይችል ይሆናል፤ ወይም ባልታሰበ መንገድ የኳስ አፍቃሪው ከሰማያዊያን ጋር ሊቃረን ይችላል። እንግዲህ የአዲስ አበባ ህዝብ ስሜት እንደ አየሩ ሁኔታ በሚቀያየርበት በዚህ ወቅት ምን ሊከተል እንደሚችል መደምደም ያስቸግራል። በዚህ ቀን በሚደረገው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ፤ በአለም አቀፍ ደረጃ ሁሉም ሰው ትኩረት ሰጥቶ ይከታተለዋል። ብናሸንፍ ደስታ፤ ብንሸነፍ ሃዘን ሆኖ ይውላል። እናም በተጠየቀው መሰረት የአዲስ አበባ መስተዳድር፤ በዚህ ቀን ሰላማዊ ሰልፉ እንዲደረግ ፈቃድ ቢሰጥ፤ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የፖለቲካ ከፍታ እና ዝቅታ ውዥቀት ሊያጋጥም ይችል ይሆናል። የሆኖ ሆኖ ግንበዚህ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ አቅርቧል። ቀደም ሲል እንደገለጽነው ይህ ቀን በስፖርት አፍቃሪው ኢትዮጵያዊ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። “ስፖርት እና ፖለቲካ ቀላቀላቹህ” ተብሎ ሌላ አስቂኝ ወቀሳ ኢህአዴግ እንዳያቀርብ እንጂ፤ የተመረጠው ቀን በኢ.ኤም.ኤፍ ድረ ገጽ አዘጋጆች እይታ አወዛጋቢ እንዳይሆን ስጋት አለ። በዚያም ተባለ በዚህ፤ ሁለቱም ዜናዎች በጉጉት የምንጠብቃቸው ስለሆኑ… በኛ በኩል እንደጋዜጠኛ የሁለቱንም የፖለቲካ (ኢህአዴግ እና ሰላማዊ) እና የስፖርት (ሴንትራል አፍሪካ እና ኢትዮጵያ) ግጥሚያዎች በተናጠል ወይም አደባልቀን፤ ጠዋት እና ከሰአት በኋላ እንዘግባለን።

ከላይ እንደገለጽነው… ዜናውን ካቀረብነው በኋላ ማስተካከያ እንድናደርግ ተጠይቋል። ይኸውም ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን የጠራው በኢትዮጵያ ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ሲሆን፤ ጨዋታው ደግሞ ከሰአት በኋላ በኢትዮጵያ 10፡00 ጀምሮ ይተላለፋል (4፡00PM)።  (በርግጥ ፊሽካ ተነስፍቶ ጨዋታ የሚጀመረው ከሰአት በኢትዮጵያ አቆጣጠር 10:30 ላይ ነው) ስለዚህ በመሃል ሰፊ የሰአት ልዩነት እንዳለ ተገልጿል።  “ሰልፉ እና ጨዋታው እርስ በርስ አይቃረኑም” ተብሏል። ይህንን በሌላ በኩል የተሰጠን አስተያየት  መጨመር አስፈላጊ በመሆኑ፤ ዜናውንም ሚዛናዊ ስለሚያደርገው ተጨማሪውን ሃሳብ አክለንበታል።

ለማንኛውም  የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ የሚከተለው ነው። ለመንግስት ያገቡትንም ደብዳቤ ከዚሁ ዜና ጋር አያይዘናል።

የፓርቲው አመራር አባላት ወቅታዊ መግለጫ ሲሰጡ።

Advertisements
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s