የኢትዮ-ቴሌኮ. የሞባይል ተጠቃሚዎችን ጥሪ መቀበያ ድምፅ በግዳጅ አስቀየረ

በፋኑኤል ክንፉ
ኢትዮ ቴሌኮም በክፍያ የሸጣቸውን የተቀባይ የሞያል ጥሪ ማሰሚያ የሃይማኖት መዝሙሮችን በዓለማዊ ዘፈኖች መቀየሩን የቴሌ ደንበኞች ለሰንደቅ ጋዜጣ አስታወቁ። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የቴሌ ደንበኞች ለሰንደቅ እንደገለጽት፤ “አንድ ወዳጄ (ብዙዎቹ እንዳሉት) ወደ ስልኬ ሲደውል ምላሹን ለመስጠት ከኪሴ ሳወጣው፣ የሞባይሌ የመቀበያ መዝሙር ተቀይሮ “ቻልኩበት ዘንድሮም ቻልኩበት፤ የኑሮ አያያዙን እኔም አሁን አወኩበት…የሚለውን ዘፈን ስሰማ ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልኩም። የጥሪ መቀበያዬ ከቴሌበክፍያ መዝሙር ማድረጌን ተጠራጠርኩ። በርግጥ መዝሙር ነበር። አማራጭ አልነበረኝም ወደ ሰንደቅ ጋዜጣ ደወልኩ”  ሲሉ ለዝግጅት ክፍላችን አስረድተዋል። የኢትዮ ቴሌኮም የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ ስለጉዳዩ በስልክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ የመቀበያ ጥሪዎችን ለደንበኞቻችን አገልግሎት መስጠት በሙከራ ፕሮጀክት የያዝነው ነበረ ካሉ በኋላ፤ ከሰጠናቸው አገልግሎቶች ውስጥ የዓለማዊ እና ሃይማኖታዊ ሙዚቃዎችና መዝሙሮች እንደነበሩ ይታወቃል። ይህን አገልግሎት ለጊዜው አቁመን የአገልግሎቱን አሰጣጥ ሁኔታና ተፅዕኖዎቹን እየገመገምን እንገኛለን። ይህ እንደተጠናቀቀ አገልግሎቱን በተመለከተ የምንደርስበትን ውሣኔ እናሳውቃለን ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ያነጋገርናቸው አንድ ከፍተኛ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ፤ “ከመብት አንፃር ማንም የመሰለውን የጥሪ መቀበያ ድምጽ መጠቀም ይችላል። ሆኖም ግን ሞባይል በሁሉም ስፍራ በተንቀሳቃሽነት የሚገኝ የመገናኛ መሳሪያ ከመሆኑ አንፃር ጥንቃቄ መውሰዱ ተገቢ ሊሆን ይችላል። በተለይ በመዝናኛ ቦታዎች፣ በታክሲ ውስጥ፣ በስራ ቦታ ላይ የሞባይል ጥሪዎች ለስለስ ያሉ ክላሲካል ቢሆኑ ይመረጣል። ሰዎች የተለያየ እምነት ያላቸው ከመሆኑ አንፃር የሃይማኖት መዝሙሮች በተለያዩ ስፍራዎች የተለያየ ስሜት ስለሚፈጥሩ አይመከሩም።” አያይዘውም፤ “ለዚህ ማረጋገጫ ከውጭ የሚገቡ ኦርጅናል የሞባይል ስልኮችን ብንወስድ በአብዛኛው በለስላሳ ክላሲካሎች የሚዘጋጁ የመቀበያ ድምፆችን ነው የምናገኘው። ይህ የሚሆነው አብዛኛው ተጠቃሚን በማይረብሹበት ሁኔታ መቀበያ ድምፆችን ለማዘጋጀት የኮሚኒኬሽን ሳይንሱ ስለሚመክር ነው። ስለዚህም ኢትዮ ቴሌኮም መጀመሪያውኑ የሃይማኖት መዝሙሮች ለመቀበያ ጥሪ መሸጥ አልነበረበትም። ተገቢ አልነበረም ብሎ አሁን እንኳን ቢያምን፣ ለደንበኞቹ በማሳወቅ የሚፈልጉትን አይነት የመቀበያ ጥሪ አማራጭ ማቅረብ ነበረበት። ቴሌ እርምጃውን የወሰደበት መንገድ ግን አገልግሎትከሚሰጥ ተቋም የሚጠበቅ አይደለም” ሲሉ ባለሙያው ለሰንደቅ ጋዜጣ አስተያየታቸውን 

Advertisements
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s