የድርጅት የአባልነት ፎርም ያልሞሉ 75 ተቀጣሪዎችን በፌደራል አባረረ

አየር መንገድ የድርጅት የአባልነት ፎርም ያልሞሉ 75 ተቀጣሪዎችን በፌደራል አባረረ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያየ የስራ መስክ በኮንትራት ሰራተኝነት ተቀጥረው ከዛሬ አራት አመታት በፊት ሲሰሩ የነበሩ 75 ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ በአስተዳደሩ ‹‹የኢህአዴግ አባል የሚያደርጋቸውን ፎርም እንዲሞሉ ተጠይቀው የሚበዙት የእንጀራ ገመዳቸው እንዳይበጠስ በመስጋት ፎርሙን በመሙላት የታዘዙትን ያደርጋሉ፡፡
ስራ በብቃት እንጂ የአባልነት መመዘኛ መሆን እንደማይገባው አቋም የያዙት ጥቂት ህሊና አደር ሰራተኞች ቂም ተቋጥሮባቸው እድገትና የደሞዝ ጭማሪ ተከልክለው በመስራትና ባለ መስራት ለወራት ከቆዮ በኋላ ዛሬ ማለዳ በስራ ገበታቸው እንደተገኙ የፌደራል የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች 75ቱን በመምረጥ ልናነጋግራችሁ እንፈልጋለን ይሏቸውና ወደ አንድ ቢሮ ይወስዷቸዋል‹‹ማንነታችሁን አጣርተናል ስለዚህ ከአሁን ወዲህ የዚህ ድርጅት ሰራተኞች ባለመሆናችሁ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ››ይሏቸዋል፡፡
በገዛ አገራቸው የድርጅት አባል ባለመሆናቸው ብቻ ለህገ ወጥ ስንብት የተዳረጉት ኢትዮጵያዊያኑ ግቢውን አንለቅም ቢሉ ምን እንደሚከተላቸው በመረዳታቸው የተባሉትን ተቀብለው ግቢውን ለቀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በአየር መንገዱ ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ መልኩ ከፎረምና ከሊግ በመጡ ወጣቶች እንዲተኩ መደረጋቸው አይዘነጋም፡፡የጉድ አገር ያለችው ማን ነበረች?
Nationality destroyer news
posted by Aseged Tamene
Advertisements
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s