አረ ወይኔ ምን አይነት ዱርዬ መንግስት ነው ያለን….!!!!!!

እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው ጊዜ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ተከታይ የሆነ ሌላ ሰልፍ አዘጋጅቷል፡፡ ለዚህም የሚመለከተውን አካል ለማሳወቅ ማመልከቻውን ማስገባቱን ሰምተናል፡፡ የሚደንቀው በዛው ቀን የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሚባል አካል… “በሀይማኖት ሽፋን ሰላማችንን ለማደፍረስ ጥረት ያደርጋሉ” ያላቸውን አካላት ሊቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ የሚል ዜና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሰማን….!

ሁለቱም ወገኖች ሰልፍ ሲወጡ ሊጋጩ ይችላሉ፡፡ ያኔም ይሄንን የሸረበው የኢህአዴግ ባለስልጣን እቤቱ ቁጭ ብሎ “ሙድ” ሊይዝ ነው ማለት ነው፡፡ በእውነት ይሄ ትልቅ ውንብድና ነው፡፡

እውነት እውነት እላችኋለሁ ይሄ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ አይመጥንም፡፡ በጣም ይጠበናል… እንዴትም ብናደርገው የሚሆነን አልመስልህ ብሎኛል፡፡ ማነው ጥበበኛ መንግስቴን ሰፋ አድርጎ የሚሰፋልን… አለበለዛ እንጃልን! እያልን ለማማረርም ተገደናል፡፡

ተስፋዬ ገብረአብ ሲነግረን… ያኔ… ደርግ የኤርትራ አባቶችን ለውትድርና መልምሎ ከገዛ ልጆቻቸው ጋር ሊያዋጋቸው ሙከራ አደረጎ ነበር፡፡ አባቶቹን ካስታጠቀ በኋላ የውጊያው ቦታ እና ሰዓት ላይ ሲደርሱ የገዛ ወገኖቻቸው ላይ ተኩሱ ብሎ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ነገር ግን አባቶቹ ወደ ልጆቻቸው ወደ ታጋዮቻቸው ሳይሆን ወደ ሰማይ ተኮሱ ነገሩ የገባቸው የሻቢያ ታጋዮችም ወደላይ የአፀፋ ተኩስ ተኮሱ፡፡ እናም አንድም ሳይነካኩ ጦርነቱን ሰርግ አስመሰሉት፡፡

ማን ያውቃል ኢህአዴግዬ ካሰበችው በተቃራኒው ሰልፈኞቿ ልክ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፈኞች “የፍትህ ያለ” ብለው አብረው ይጮሁ ይሆናል!

የምር ግን በመንግስቴ እንደዛሬ የተበሳጨሁባቸው ጊዜያት በጣም ጥቂት ቀናትን ናቸው…. ግፋ ቢል አንድ ሶስት መቶ ጊዜ ብቻ ቢሆን ነው… ይሄኛው አንድ ሺህ ሶስት መቶ አንድኛ ሆነ ማለት ነው…. ሆሆይ ጉድ!!!

Advertisements
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s