•  
    በማንኛውም የህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ መውደቅም ሆነ ማዳለጥ ያለ ነው። መነሳት አንድ የጠንካራ ሰው ነገር ነው፡፡ ደግሞ መውደቅ ፣ሆኖም እዚያው ቦታ ላይ መውደቅ አሳዛኝ ነው፡፡ ቀጭንና አዳላጭ የሆኑ የትግል መንገዶች ብዙ ናቸው፡፡ መሳለጫ እየመሰሉ የማያሳልፉ መኖራቸውን ያልተገነዘበ ታጋይ፣ ደጋግሞ መውደቅ አይቀርለትም! እንግሊዙ የታሪክ ተመራማሪ ስለፈረንሳይ የንጉስ ናፖሊዮን ሶስተኛው እንዲህ ሲል ፅፏል፡- “የአንድ አገር መሪ አደገኛ ነገር ነው ብዬ የማስበው የታሪክ ተማሪ መሆኑን ነው። እንደታሪክ ተማሪዎች ሁሉ መሪውም ካለፈው ስህተቱ የተማረው እንዴት አዲስ ስህተት እንደሚሰራ ነው!” ይላል፡፡ ለእኔ ብለህ ስማ ነው፡፡ ገጣሚው፣ፈላስፋውና ሃያሲው ሳሙኤል ቴይለር ኮልሪጅ፤ ደግሞ፤ “ሰዎች ከታሪክ ለመማር ቢችሉ ኖሮ፤እንዴት ያለ ትምህርት ባገኙ! ሆኖም አንድን ነገር ሙጭጭ ብሎ ከመውደድና በይዞታነት የያዝነው ፓርቲ ዐይናችንን ከማሳወሩ የተነሳ፤ ልምድ የሚያበራልን ማሾ ያለፍነውን ማዕበል ብቻ ይሆናል” ይለናል፡፡ ለእኔ ብለህ ስማ ነው ጐበዝ!
    ሔገል የባለው ጀርመናዊ ፈላስፋ በበኩሉ፤ “ልምድና ታሪክ የሚያስተምሩን አንድ ነገር አለ፡፡ ይሄውም ህዝቦችና መንግሥታት ከታሪክ በፍፁም እንደማይማሩ ነው፡፡ አሊያም ደግሞ ከታሪክ ባገኙት ትምህርት መሠረት ምንም እርምጃ አለመውሰዳቸው ነው፤ ይለናል፡፡ ለእኔ ብለህ ስማ ነው ጐበዝ! “ህይወት ሰዎች ሲሞቱ አስቂኝ መሆኗን የማታቆመውን ያህል፤ ሰዎች ሲስቁም ህይወት ኮስታራ መሆኗን አታቆምም፡፡” በርናርድ ሾው ነው ይሄን ያለው፡፡ ዕውነቱን ነው፡፡ የዛሬው መስቀል ደመራ በየትም ወደቀ በየት፤ ከላይ የጠቀስናቸው ጥቅሶች የበዓሉ ስጦታ ይሁኑ! “ትላንትና ማታ ቤትህ ስትገባ እንቅፋት የመታህ ድንጋይ ዛሬ ማታም ከደገመህ፤ ድንጋዩ አንተው ነህ!” – የምንለው ዓመቱን በፍቅር፣ ሰላምና በብርሃን እንድንገፋው ነው!
    ብሔራዊ እርቅ ይቅደም
    ብሔራዊ እርቅ ይቅደም
Advertisements
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s