የኢትዮጲያ ህዝብ እድሜ ልክ ተፈረደበት

ህዝብ እስካሁን እየኖረ ያለው ማሰብ በማይችሉ ራስ ወዳዶችና ስልጣን ሞቴዎች ስር ሲሆን እነኚሁም እየተፈራረቁ ገዝተውታል ሳይሆን ተጫውተውበታል። ታዲያ ህዝቡ የዱሮ አባቶች በሰሩት ታሪክ አሸሸም ገዳሜ እያለ፤ እንዲህ ነበር ያኔ ያደረጉት በሚል ዲስኩር መኖሩን ከያዘው ዓመታት አልፈው ዘመን ተቆጠረ መሰለኝ። የያኔዎቹ ናቸው ይችን የምንደሰኩራትን ወሬ እንኳን ትተውልን ያለፉት ለዛውም በመኃይምነት አዕምሮአቸው። የነሱን ውለታም ሆነ ጥፋት ሾላ በድፍኑ እናድርገውና ጥሩ ነገራቸውን ወስደን ማመስገኑን ብንቀጥል ባይ ነኝ። ነገሩ ግን እንዲህ ነው፤ አሁን ባለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን የተማረ በዛ በተባለባት ኢትዮጲያ ሃገሪቷ ውጥንቅጧ ጠፍቶ፣ ዜጎቿ ሃገራቸውን በጠሉበት ሰዓት ሁሉም ውቅያኖስ ተሻግሮ መጓዝ የሚያልምባት ሃገር እንድትሆን ያደረጓት ወያኔዎች ይኸው ተቆጣጠርን ካሉባት ጊዜ ጀምሮ በሃገሪቷ ላይ ያለው ህዝብ በሮሮና በለቅሶ መኖሩን ተያይዞታል። ለእነርሱ እንዲህ ነው ብትሏቸው ድንጋይና አስፋልት የሚያሳዩአችሁ ምስክርነት ነው ግና እርሱ የኛ ሳይሆን የአሜሪካንና የምዕራቡን ደህንነት ለመጠበቅ በሚደረገው የልመና ዘመቻ የተገኘ ለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። እነርሱ ስለ ሰው መበደል ምን ገዷቸው፤ የሚለምኑት ግን በኛ ስም።
እኔ በዕድሜዬ መስማት የተሳናቸው እንጂ መብላት የተሳናቸው ህዝቦችን አላውቅም። በሃገራችን ግን በሚሊዮናት የሚቆጠሩት መብላት ከተሳናቸው ውለው አድረዋል። ወሬ አይበላ፣ ሪፖርት ስንዴ አይሆን፣ 11 በመቶ የበቆሎ ቂጣ ሆኖ አይበላ!! ኧረ ሰዎች በአውሬዎች እየተበላን ነው!!! እስቲ ታዲያ አወዳድሩታ ያኔ ሳይማሩ አገሪቷን ጠብቀው አስረከቡን እኛ ደግ…

 

See More

Advertisements
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s