Thursday, October 24, 2013

በራያ ቆቦ በመኪና አደጋ 26 ሰዎች ሞቱ

 
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 14፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ትናንት በደረሰ የመኪና አደጋ የ31 ሰዎች ህይወት ወዲያው  ሲያልፍ በቀሪዎቹ ላይ ከባድ አደጋ ደርሷል።
አደጋው የደረሰበት አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢስ የመጫን አቅሙ 24 ሰው ሲሆን ነገር ግን 43 ሰዎች ጭኖ ከቆቦ ወደ ዞብላ ሲጓዝ ነበር።
ከቆቦ 24 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከርቦ በምትባለው አካባቢ ሲደርስ 200 ሜትር ጥልቀት ካለው ገደል ውስጥ በመግባተቱ ነው አደጋው የደረሰው።
የጉዳቱ መጠን ከፍ ያለ በመሆኑም የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችለ ተገልጿል።
አሽከርካሪና ረዳቱ  በወቅቱ ያመለጡ ቢሆንም ፥  በአሁኑ ወቅት ግን አሽከርካሪው  በቁጥጥር ስር መዋሉ  ተመልክቷል።
 
Advertisements
Aside | Posted on by | Leave a comment

EPPF Says It Has Attacked Regime Forces

SS
October 24, 2o13
The rebel group, Ethiopian People’s Patriotic Front (EPPF) says killed 7 and wounded dozen near Sinar, Armacheho, North Western Ethiopia on October 18, 2013.
EPPF’s Radio also reported that the rebels had sized several weapons making them gain military and political victory over the government.
The Front claims that it fights to bring regime change in Ethiopia. EPPF had unleashed similar attacks on government securities in the same region before, most of which the government itself admitted.
The Front has been engaged in small scale conflicts with the government for the past decade now.
debirhan.com

Posted in Uncategorized | Leave a comment

 

አርቲስት ማለት በተፈጥሮ ያገኘውን ጸጋ ተጠቅሞ መልእቱን ማስተላለፍ የሚችል በስዕል፣ በሙዚቃ፣ በስነጽሁፍ፣ በቲያትር… ሊሆን ይችላል፡፡ አርቲስቶችም ይህን ጸጋ ተጠቅመው ሰዎችን በዙሪያቸው በማሰባሰብ ህልሞቻቸውን ወይም ያለውን ነባራዊ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ጉዳዮች እያነሱ ሰላምን አንድነትን ፍቅርን ይሰብካሉ፤ በስራዎቻቸው ሪፖርት ያደርጋሉ፤ ይተንትናሉ፤ ይቀሰቅሰቀሉ፤ አንዳንድ ድብቅና የታፈኑ ጉዳዮችን ያላቸውን ፀጋ ተጠቅመውም ያጋልጣሉ፤ ብቻ በአጠቃላይ አርቲስቶች ከማዝናናት በዘለለ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ በሚፈጠር እድገት ትልቅ ሚና ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡

በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ምስቅልቅል ባለ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ በምትገኝ ሀገር ከሁሉ በተሻለ አርቲስቶች ህብረተሰቡን የማረጋጋትና የማቀራረብ እንዲሁም ውስጣዊ ሰላሙን እንዲያገኝ የማስቻል፤ ሀገሪቷንም ነባራዊ ሁኔታ የማሳየትና መፍትሄዎችን እስከመጠቆም ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እንዳለመታደል ሆኖ ከማንም በከፋ እንደውም አርቲስቶቻችን ለማህበረሰቡ ማበርከት የሚገባቸውን አገልግሎት ትተው፤ ጭራሽ ለየትኛውም ወጣት እና ህጻናት አርአያ መሆን የማይችሉ ንዋይ አምላኪዎች ሆነው እነሱ ራሳቸው ችግር እየሆኑብን ተቸገርን፡፡ እንዲህ እንዳወራ ያደረገኝ ባለፈው ሳምንት ይድነቃቸው ከበደ “በ1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና በ12 ድራፍት ብርጭቆ – እውነትና ከሕደት…” ብሎ የጻፈውን እንዳነበብኩ በእያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ ያለው የመንፈስ ክስረትና ክሽፈት ከስርአቱ ጋር የሚደረገውን ትግል ምን ያህል ከባድ እንዳረገው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡

አርቲስት ደበበ እሸቱ (ጋሽ ደቤ) በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት ካሉት አርቲስቶ…Continue Reading

 

አርቲስት ማለት በተፈጥሮ ያገኘውን ጸጋ ተጠቅሞ መልእቱን ማስተላለፍ የሚችል በስዕል፣ በሙዚቃ፣ በስነጽሁፍ፣ በቲያትር… ሊሆን ይችላል፡፡ አርቲስቶችም ይህን ጸጋ ተጠቅመው ሰዎችን በዙሪያቸው በማሰባሰብ ህልሞቻቸውን ወይም ያለውን ነባራዊ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ጉዳዮች እያነሱ ሰላምን አንድነትን ፍቅርን ይሰብካሉ፤ በስራዎቻቸው ሪፖርት ያደርጋሉ፤ ይተንትናሉ፤ ይቀሰቅሰቀሉ፤ አንዳንድ ድብቅና የታፈኑ ጉዳዮችን ያላቸውን ፀጋ ተጠቅመውም ያጋልጣሉ፤ ብቻ በአጠቃላይ አርቲስቶች ከማዝናናት በዘለለ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ በሚፈጠር እድገት ትልቅ ሚና ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ምስቅልቅል ባለ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ በምትገኝ ሀገር ከሁሉ በተሻለ አርቲስቶች ህብረተሰቡን የማረጋጋትና የማቀራረብ እንዲሁም ውስጣዊ ሰላሙን እንዲያገኝ የማስቻል፤ ሀገሪቷንም ነባራዊ ሁኔታ የማሳየትና መፍትሄዎችን እስከመጠቆም ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እንዳለመታደል ሆኖ ከማንም በከፋ እንደውም አርቲስቶቻችን ለማህበረሰቡ ማበርከት የሚገባቸውን አገልግሎት ትተው፤ ጭራሽ ለየትኛውም ወጣት እና ህጻናት አርአያ መሆን የማይችሉ ንዋይ አምላኪዎች ሆነው እነሱ ራሳቸው ችግር እየሆኑብን ተቸገርን፡፡ እንዲህ እንዳወራ ያደረገኝ ባለፈው ሳምንት ይድነቃቸው ከበደ “በ1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና በ12 ድራፍት ብርጭቆ – እውነትና ከሕደት…” ብሎ የጻፈውን እንዳነበብኩ በእያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ ያለው የመንፈስ ክስረትና ክሽፈት ከስርአቱ ጋር የሚደረገውን ትግል ምን ያህል ከባድ እንዳረገው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ አርቲስት ደበበ እሸቱ (ጋሽ ደቤ) በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት ካሉት አርቲስቶች ግንባር ቀደሙና አንጋፋው ስለመሆኑ ለመከራከር መሞከር ሞኝነት ነው፡፡ ጋሽ ደቤ የሰራቸውን ስራዎች መጨረሻ ላይ በከፊል ለማስቀመጥ እሞክራለሁ ግን፡፡ ግን ዛሬ “አርቲስት” ነን የሚሉ ሰዎች ይህንን አንጋፋ የሙያ አባታቸው እና መምህራቸው ፤ እነ ጋሽ ደበበ በስንት መስዋዕትነት የከፈቱላቸውን መንገድ ተጠቅመው ዛሬ ለደረሱበት ደረጃ ሲያበቋቸው ባያመስግኗቸው እንኳ ምናለ እውቅና እንኳ ባይነፍጓቸው፡፡ ጋሽ ደቤ ስንት ትያትሮችን ያዘጋጀበት የተወነበት በስራ አስኪያጅነት የመራበትእና ያስተማረበት ብሔራዊ ትያትር በህይወት ያሉ እና የሌሉ አንጋፋ አርቲስቶችን ለማመስገንና ለማወደስ ያዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ጋሽ ደቤን ባለው የፖለቲካ ተሳትፎ ምክንየት እንዳይገኝ እና ስሙ እንዳይጠራ በስምምነት መወሰናቸው፤ ከመካከላቸውም ይህንን ተቃውሞ አንድም አርቲስት ድምጹን ለማሰማት አለመሞከሩ ያለንበት ማህበራዊ ዝቅጠት ደረጃን ዘግናኝ አድርጎታል፡፡ ጋሽ ደቤ በግል ህይወቱ ለማንኛውም ወጣት አርአያ መሆን የሚችል ጠንካራ ቤተሰብ ያለው የተረጋጋ እና ለህሊኒው የሚገዛ ስለመሆኑ የኔ ዲስኩር ሳይሆን እየኖረ ያለው ህይወት ምስክር ነው፡፡ ጋሽ ደቤ እንደሌሎቹ አርቲስት ነን ባዮች ቢያጎበድድ ምናልባትም ሀገሪቷ ውስጥ ካሉ ሚሊየነሮች ተርታ ተሰላፊ እንደ ሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡ በጅብ ሊቀመንበር በጦጣ ጸሀፊ አንቺ ሰባ ሰባት ቶሎ ቶሎ እነፊ፤ ነበር ያለው የወሎ ሰው፤ ጋሽ ደቤ ለታሪክ የሚተላለፉ ህያው ስራዎች ሰርቷል እነዚህን ስራዎቹን በምንም ሊፍቋቸው እና ሊያጠፏቸው አይችሉም፡፡ የእውነት ዘመን ሲመጣ ለአደባባይ ይበቃሉ፡፡ አያድርገውና ጋሽ ደቤ የሆነ አደጋ ላይ ቢሆን እነዚህ የብሔራዊ ትያትር “አርቲስቶች” የጋዜጦችና መጽሔቶች የሽፋን ገጾችን እንዴት እንደሚያጨናንቁ አስቡት ዛሬ ግን የብሔራዊ ትያትር እንዳይጋበዝ ሲከለከል እንዳቸውም ድምጻቸን ለማሰማት አልደፈሩም፡፡ ነገር ግን ጋሽ ደቤ የእውነት ስራዎቹን የሚያደንቁለትና የእሱን አርአያ የሚከተሉ ወጣቶች አሉ፡፡ “አያናግረንም የያዘን አባዜ ዝም አያሰኘንም የያዘን አባዜ እንደው ፍዝዝዝዝ ያሰኘናልሳ ቅጥ አምባሩ ያጣ የቁም ሞት አባሳ፡፡” እስቲ ጋሽ ደቤ ከሰራቸው ስራዎች ውስጥ በጥቂቱ እንያቸው፤ በሃገር ውስጥ ካለው ታዋቂነትና ለሙያው ካደረገው አስተዋጽኦ ለመጠቀስ ያህል ፡- በመድረክ ላይ በቤተኪነጥበባት ወቴአትር ያላቻ ጋብቻ ተዋናይ ሮሚዎባ ዡልየት ተዋናይ ጠልፎ በኪሴ ተዋናይም አዘጋጂም ዳንዴው ጨቡዴ ›› ዘ ጌም ኦፍ ቼዝ (በእንግሊዝኛ) ተዋናይ ኦቴሎ (በአንግሊዝኛ) ተዋናይም አዘጋጂም አዳ ኦክ አራክል (በእንግሊዝኛ)ከሎ.ጸ.ገ.መ ተዋናይ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ(ብሔራዊ) ቴአትር የበጋ ሌሊት ራዕይ ተዋናይ አንድ ዓመት ከአንድ ቀን ተዋናይ እናት ዓለም ጠኑ ተዋናይ ኪንግ ሊር ተዋናይ ዋናው ተቆጣጣሪ ተዋናይ ጠያቂ ተዋናይ አዘጋጅ በቀይካባ ስውር ደባ አዘጋጅ ተሓድሶ አዘጋጅ የአዘውንቶች ክበብ አዘጋጅ ተዋናይ በሃገር ፍቅር ቴአትር ጠልፎ በኪሴ አዘጋጅ/ተዋናይ የወፍ ጎጆ ተዋናይ ኪንግ ሊር ተዋናይ የቬኒሱ ነጋዴ ተዋናይ ናትናኤል ጠቢቡ ተዋናይ ድብልቅልቅ ተርጓሚ/ ተዋናይ ማዕበል ተርጓሚ አዘጋጅ በፊልም በሃገርና በዓለም አቀፍ ዘ ሴይለር ፍሮም ጂብራልታር ሻፍት ኢን አፍሪካ ጉማ ዚ አፍሪካን ስፓይ ዜልዳ አፍሪካ ዘግሬቭ ዲገር ዘ ግሬት ሪቤሊየን እነዚህ ለምሳሌ ያህል የቀረቡ እንጂ የደበበ ስራዎች በርካቶች ናቸው፡፡ ከመድረክና ፊልም ስራዎቹ ባሻገር ተማሪዎችም አሰልጥኗል፡፡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን በብሔራዊ ቴአትር የተዋንያን ስልጠና ማዕከል ሲያቋቁሙ ከመምሃራኖቹ መሃልና በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው መምህር ደበበ ሲሆን ለተማሪዎቹም መማርያ እንዲሆን የተረጎመው የስታንስላቭስኪ የተዋናይ ሀሁ ለበርካታዎች የሙያ ተማሪዎች የሙያቸው ፊደል መቁጠርያ ሆኖ ይገ ኛል፡፡ በትርጉም በኩልም ደበበ ከቴአትር ያልታመመው በሽተኛ ድብልቅልቅ ጎርፉ ከመጽሐፍ ደሞ የዳዊት ወልደጊዮርጊስን የደም እንባ የራሱን ወጥ ሥራ በተመለከተ የእምነቴ ፈተና ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው ደበበ ለአፍሪካ ጥበብ ያለውን አመለካከትና ግንዛቤ ከቅኝ ገዢዎች ትርጓሜ ለማውጣትና ሶስተኛው ዓለም ኋላ ቀር ሲባልም በኤኮኖሚና በቴክኒዮሎጂ እንደሆነ፤ ይህም የሆነው ነጩ የአፍሪካን የዋህነት፤ እንግዳ ተቀባይነትና ሩህሩህነት መንጠላጠያ በማድረግ ቅኝ አድርገው ህሊናውን ስለዘጉበትና ስላሰሩት መሆኑን፤በባህል በኩል ግን ጨርሶ ሊደርሱበት የማይችሉትና ሊያጠፉትም ያደረጉት ሙከራ ዋጋ ቢስ ሆኖ እንደቀረ የሚያስረዳ ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ ተቀባይነትን አግኝቶ ድል ያደረገና፤ ቀደም ሲል የጀመረውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል በ1985 ዓ/ም እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በርሊን ላይ በተካሄደው የዩኔስኮ የባህል(አይ ቲ አይ) ኢንተርናሽናል ቴአትር ኢትዮጵያን ወክሎ በመገኘት በአፍሪካ ውስጥ የመጀመርያው ፕሮፌሽናል ቴአትር ቤት የሃገር ፍቅር ቴአትር መሆኑን በማስረጃ አስደግፎ ተቀባይነትን አገኘ፡፡ በዚሁ ዓመት የዩኔስኮ የባሕል ክፍል አይ ቲ አይ የአፍሪካ ተጠሪ ሆኖ በመመረጥ፤ በዚያው ዘመን ዝምባብዌ ላይ በሚካሄደው ቴአትር ለልማትና ዕድገት ወርክሾፕ ላይ በመሪነት እንዲገኝ በዩኔስኮ ተወክሎ በመሄድ ወርክሾፑን በአጥጋቢ ችሎታውና የአመራር ብቃቱ ከመፈጸሙም ባሻገር ለብዙ ጊዜ ተሞክሮ ሲወድቅ ሲነሳ የነበረውን የአፍሪካ የመድረክ ባለሙያዎች ማሕበርን አስተባብሮ በማቋቋም የማሕበሩም መስራች ፕሬዜዳንት ሆኖ ለ12 ዓመታት መርቷል፡፡ አሁንም መስራች ፕሬዛዳንት በመባል ይጠራል፡ ደበበ በችሎታውና በብቃቱ በማስተባበር ችሎታው ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የቴአትር ኢንሳይክሎፒዲያን ለማዘጋጀት ሲወስን ደበበንም አፍሪካን በመወከል የኤዲቶርያል ቦርድ አባል አድርጎ መድቦት ሥራውን በሚገባ ተወጥቷል፡፡ ደበበ ቴአትር ለልማትና ለእድገት በሚል የሚታወቀውን የቴአትር ዲሲፕሊን ስልጠና ለበርካታ ሃገራት ባለሙያዎች ያስተማረ ሲሆን በርካታ ወርክሾፖችም በየሃገራቱ እየተጋበዘ መርቷል፡፡ ይሀን ዘዴ ካዋቀሩትም አምስት አፍሪካዊ ባለሙያዎች አንዱ ደበበ ነው፡፡ ወርክሾፕ የሰጠባቸው ቦታዎች፤ ታንዛኒያ፤ኡጋንዳ፤ኬንያ፤ማላዊ፤ኮንጎ ብራዛቪል፤አይቮሪ ኮስት፤ ካሜሩን፤ ናይጄርያ፤አይርላንድ፤ብራዚል፤ሰሜን አሜሪካ፤እንግሊዝ፤ ኩባ፤ በርሊን፤ካናዳ ይገኙበታል፡፡ ደበበ ላለፉት ከ40 በላይ ዓመታት በቴአትር ጥበብ ውስጥ ኖሮ በ1995 በተካሄደው ሃገራዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ‹‹ቀስተደመና›› የፖለቲካ ፓርቲን ተቀላቅሎ፤ በኋላም ቅንጅት ሲፈጠር የምክር ቤት አባልና የሕዝብ ግንኙነት በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ቅንጅትን ለድል ያበቃ፤ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዝግጅቶቹ ገዢውን ፓርቲ ያንበረከኩና ቅንጅትና ያገዘፉ ነበሩ፡፡በዚህም ከሌሎች አመራሮች ጋር ለአንድ ዓመት ከአስር ወራት ለእስር ተዳርጓል፡፡ እንዲሁም በ2002 በድጋሚ ለአንድ አመት ታስሮ ተፈቷል፡፡ በሱ ሙያ የተሰለፉ ‹‹አይተነው ጊዜ›› ሲሉ እሱ ግን ‹‹እኔም ድርሻ አለኝ›› በማለት ቤተሰቡን፤ ምቾቱን፤ ተድላውን፤ ሁሉ ችላ በማለት ክግል ይልቅ ለህብረተሰቡ፤ ከራሱ ይልቅ ለወገኑ በመወገን የተሰለፈ ብቸኛ የጥበብ ሰው ነው፡፡አንዳንዶች ሹመትና ገንዘብ ሲያታልላቸው፤ እሱን ያታለለው ግን ነጻነት ፍትህና ዴሞክራሲ ከሰብአዊ መበት መከበር ጋር ነው፡፡ለዚህም ነው ከማንም በላይ ሕዝባዊ የክብር ዘውድ የተደፋለት፡፡ ዛሬ ያንን ዘውድ ደፍቶ ባናየውም ታሪክ ግን እንዳለበሰው ይኖራል አንድ ቀን ይሀም ይፋ ሆኖ ይከበራል፡፡ ደበበ በሃገሩ ለመሸለም ባይበቃም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን ለሽልማቶች የበቃ ባለሙያ ነው፡፡ለዚሁ የሙያ አስተዋጽኦ ክፍተኛው ክብሩ በአትላንታ ጆርጂያ ኖቬምበር 24 የደበበ እሸቱ ቀን ተብሎ እንዲሰየም የከተማው ምክር ቤት ማጽደቁ ነው፡፡ ጋሽ ደቤ ጋደኛም ሚስትም ከሆነችው ከአልማዝ ደጀኔ ጋር 4 ልጆች እና 6 የልጅ ልጆች ያሉት ሲሆን ሰኔ 2005 ዓ.ም 40ኛ ዓመታቸውን ከልጆቻቸው እና የልጅ ልጆቻቸው በተገኙበት አክብረዋል፡፡ ፍቅር ሰላም እና ጤና ለጋሽ ደቤ አብዝቶ ይስጥልን! (የጋሽ ደቤን ስራዎች በተመለከተ ወንድወሰን አንድአርጋቸው 2001 ዓ/ም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለመመረቂያ ካዘጋጀው ሥራ እንዲሁም “የእምነቴ ፈተና “ ከሚለው የጋሽ ደቤ መጽሐፍ መግቢያ ላይ አለምፀሀይ ወዳጆ ከጻፈችው ምስክርነት የተገኘ ነው)

Aside | Posted on by | Leave a comment

የኢትዮጲያ ህዝብ እድሜ ልክ ተፈረደበት

ህዝብ እስካሁን እየኖረ ያለው ማሰብ በማይችሉ ራስ ወዳዶችና ስልጣን ሞቴዎች ስር ሲሆን እነኚሁም እየተፈራረቁ ገዝተውታል ሳይሆን ተጫውተውበታል። ታዲያ ህዝቡ የዱሮ አባቶች በሰሩት ታሪክ አሸሸም ገዳሜ እያለ፤ እንዲህ ነበር ያኔ ያደረጉት በሚል ዲስኩር መኖሩን ከያዘው ዓመታት አልፈው ዘመን ተቆጠረ መሰለኝ። የያኔዎቹ ናቸው ይችን የምንደሰኩራትን ወሬ እንኳን ትተውልን ያለፉት ለዛውም በመኃይምነት አዕምሮአቸው። የነሱን ውለታም ሆነ ጥፋት ሾላ በድፍኑ እናድርገውና ጥሩ ነገራቸውን ወስደን ማመስገኑን ብንቀጥል ባይ ነኝ። ነገሩ ግን እንዲህ ነው፤ አሁን ባለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን የተማረ በዛ በተባለባት ኢትዮጲያ ሃገሪቷ ውጥንቅጧ ጠፍቶ፣ ዜጎቿ ሃገራቸውን በጠሉበት ሰዓት ሁሉም ውቅያኖስ ተሻግሮ መጓዝ የሚያልምባት ሃገር እንድትሆን ያደረጓት ወያኔዎች ይኸው ተቆጣጠርን ካሉባት ጊዜ ጀምሮ በሃገሪቷ ላይ ያለው ህዝብ በሮሮና በለቅሶ መኖሩን ተያይዞታል። ለእነርሱ እንዲህ ነው ብትሏቸው ድንጋይና አስፋልት የሚያሳዩአችሁ ምስክርነት ነው ግና እርሱ የኛ ሳይሆን የአሜሪካንና የምዕራቡን ደህንነት ለመጠበቅ በሚደረገው የልመና ዘመቻ የተገኘ ለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። እነርሱ ስለ ሰው መበደል ምን ገዷቸው፤ የሚለምኑት ግን በኛ ስም።
እኔ በዕድሜዬ መስማት የተሳናቸው እንጂ መብላት የተሳናቸው ህዝቦችን አላውቅም። በሃገራችን ግን በሚሊዮናት የሚቆጠሩት መብላት ከተሳናቸው ውለው አድረዋል። ወሬ አይበላ፣ ሪፖርት ስንዴ አይሆን፣ 11 በመቶ የበቆሎ ቂጣ ሆኖ አይበላ!! ኧረ ሰዎች በአውሬዎች እየተበላን ነው!!! እስቲ ታዲያ አወዳድሩታ ያኔ ሳይማሩ አገሪቷን ጠብቀው አስረከቡን እኛ ደግ…

 

See More

Aside | Posted on by | Leave a comment

በሰሜን ጎንደር ዞን ስር የነበሩ ሁለት ወረዳዎች ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ እንዳለ ተጠቆመ –

Posted: October 21, 2013 in Uncategorized

አብረሃ ጅራ እና አብደራጊ የተባሉ ሁለት ወረዳዎች ከዚህ በፊት በአማራ ክልል ስር ነበሩ፡፡ ነገር ግን መሬቱ ባብዛኛው በቅርብ ጊዜ ከትግራይ ክልል በመጡ ገበሬዎች ተይዟል፡፡ ገበሬዎቹም አስተዳደራዊ የበላይነትን በመጠቀም ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ስብሰባ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ የጀመሩ ሲሆን ከ500 ሺህ ብር በላይም ለጉዳዩ ማስፈፀሚያ ማዋጣታቸው ተጠቁሟል፡፡ የአማራ ክልል እንኳ እምቢ ቢላቸው በፌዴራል እንደሚያስጨርሱም ተጠቁሟል፡፡

ነገር ግን የሳንጃ፣ ጠገዴ፣ ዳባትና አፎኛ ደምቢ ወደራ ነዋሪዎች የገበሬዎቹን ጥያቄ እንደሚቃወሙ የጠቀሱ ሲሆን ጥቅምት 12 በሚጠሩት ስብሰባም የንግድ ተቋማት እንደሚዘጉ፣ ስራ እንደሚያቆሙና ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደሚዘጉ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ  ፍኖተ ነጻነት

Aside | Posted on by | Leave a comment
 •  
  የሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ-ምህረት የመጀመሪያ ወር ተጠናቅቋል፤ አዳዲስ ክስተቶችም ታይተዋል፤ ያለፉት አስራ ሁለት ዓመታትንበጃንሆይ ቤተ-መንግስት ያሳለፉት ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ በኦህዴዱ ሙላቱ ተሾመ መተካታቸው አንዱ ነው፡፡ አባይ ፀሀዬና ዶ/ር ካሱ ኢላላም ከበረከት ስምዖንና ኩማ ደመቅሳ በተጨማሪ በሚኒስትር ማዕረግ የኃ/ማሪያም ደሳለኝ ‹‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር›› አማካሪ ሆነው መሾማቸው ሌላው ነው (በነገራችን ላይ ሹመቱን እንደተለመደው አይቶ ችላ ብሎ ለማለፍ የማያስችሉ ሶስት ምክንያቶች አሉ፤ የመጀመሪያው በሀገሪቱ ለአንድ የሥራ መደብ አራት ሚንስትር ተሹሞ አለማወቁ ሲሆን፤ ሌላው ተሿሚዎቹ፣ ኢህአዴግን ከመሰረቱት አራት ፓርቲዎች በኮታ የተወጣጡ መሆናቸው ነው፡፡ ሳልሳዊውና አስገራሚው ደግሞ ሰዎቹ ፖለቲከኞች እንጂ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ምሁራን አለመሆናቸው ነው)
  እነዚህ ሁሉ በግልፅ የሚታወቁ የዓመቱ መጀመሪያ ክስተቶች ናቸው፡፡ ለስርዓቱ ቅርበት ካላቸው ምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ መሠረት፣ በቅርቡ ‹ሚዲያ›ን እና ‹የይቅርታ ስነስርዓት›ን የተመለከቱ አዳዲስ አዋጆች በተወካዮች ም/ቤት ለመፅደቅ ተዘጋጅተዋል፡፡ በተለይም ‹ሚዲያው›ን የሚመለከተው አዲሱ ህግ፣ ከአምስት ዓመት በፊት ተግባር ላይ የዋለውን የ‹‹ፕሬስ አዋጁ››ን የአፋና ጉልበት ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ፣ የነበረው አንፃራዊ ጭላንጭል ጭራሽ ሊዳፈን እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ‹‹የይቅርታ አዋጁ››ም ቢሆን ጥቂት የአገዛዙ ጉምቱ ባለስልጣናት ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባላትና አንዳንድ የግል ጋዜጠኞች ብንታሰርም በይቅርታ እንፈታለን በሚል ግንባሩን እየተፈታተኑ ነው›› ሲሉ ደጋግመው መደመጣቸውን፣ ከአዲሱ ‹‹የይቅርታ አሰጣጥ እና አፈፃፀም ሥነ-ሥርአት አዋጅ›› ጋር ካያያዝነው፣ አንቀፆቹ ሊኖራቸው የሚችለውን አንድምታ መገመቱ ብዙ ከባድ አይሆንም፡፡

  http://eth-freedom.blogspot.no/2013/10/blog-post_8440.html

  The Voice of Freedom: የኢህአዴግ ቀጣይ የፖለቲካ ሴራዎች – (ተመስገ ደሳለኝ)

  eth-freedom.blogspot.com

  Freedom of Expression For All Ethiopian Peoples , NOW ! ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፣ አሁኑኑ ! Free all Ethiopian Jornalist and Political Prisoners, Stop the Persecution of Independent Press in Ethiopia, We shall prevail! Freedom! Freedom! Freedom! FREEDOM, FREEDOM !!!
   
   
   

  Like · · Share · about an hour ago · 

Aside | Posted on by | Leave a comment
 

The current situation of addis abeba

In the heart of Ethiopia’s capital, Addis Ababa, near a hotel and an Orthodox Christian cathedral, lies one of the country’s most notorious police stations, the Federal Police Crime Investigation Sector, commonly known as Maekelawi. 

Many of Ethiopia’s political prisoners—opposition politicians, journalists, protest organizers, alleged supporters of ethnic insurgencies , and many others—are first taken to Maekelawi (“central” in Amharic), after being arrested. There they are interrogated, and, for many, at Maekelawi they suffer all manner of abuses, including torture.

Police investigators at Maekelawi use coercive methods on detainees amounting to torture or other ill-treatment to extract confessions, statements, and other information from detainees. Detainees are often denied access to lawyers and family members. Depending on their compliance with the demands of investigators, detainees are punished or rewarded with denial or access to water, food, light, and other basic needs.

This report documents human rights abuses, unlawful investigation tactics, and detention conditions in Maekelawi between 2010 and 2013. For the report Human Rights Watch interviewed more than 35 former detainees of Maekelawi and their family members. Although Human Rights Watch was not able to visit Maekelawi, preventing first-hand observation of conditions and interviews with current detainees, researchers cross- checked information provided by former detainees, who were identified through various channels and interviewed individually.

Aside | Posted on by | Leave a comment