ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ………. ጦቢያን ገረመው

ይህች አነስተኛ መጣጥፍ ለታዋቂው ጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ መታሰቢያነት ትዋልልኝ፡፡ ምክንያት አለኝ፡፡ ርዕሱ በመጠኑ ተሻሽሎ የተወሰደው በእርሱ ባለቤትነትና አዘጋጅነት ይመራ ከነበረው ከምኒልክ ጋዜጣ ነው፡፡ ባጭሩ ለማስታወስ – የዛሬ 12 ዓመት ገደማ በ93 ዓ.ም ወያኔ ለሁለት ተሰንጥቃ ነበር፤ ከዚያ በፊትም በ90 አካባቢ ንፋስ ይገባባቸው እማይመስሉት ወያኔና ሻዕቢያ ባላሰቡትና ባልጠበቁት መንገድ መቃቃራቸው የሚታወስ ነው፡፡ ያኔ ወያኔ በተቸካይነትና በተሃድሶነት ተከፋፈለች በተባለበት የዘመነ ህንፍሽፍሽ ወቅት ታዲያ አንድ ጸሐፊ በምኒልክ ጋዜጣ ‹እልልልልልልልል…› በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ ልኮ ‹አስነብቦን› ነበር፡፡ የሚገርማችሁ መጣጥፉ በእልልታ ጀምሮ ያለቀውም አንድም ሌላ ቃል ሳይጨምር በእልልታ ነበር፡፡ በምናባዊነቱ እየተገረምኩ በደስታ ‹ያነበብኩት መጣጥፍ› ስለነበር መቼም አይረሳኝም፡፡ ያቺን በማስታወስ ነው እንግዲህ ለኔ የዛሬዋ መጣጥፍ ተቀራራቢ ርዕስ የሰጠሁት፡፡ 74 more words

This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a comment